መዝሙር 54 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 54 ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች፤ ዚፋውያን ወደ ሳኦል መጥተው፣ “ዳዊት በእኛ ዘንድ ተደብቋል” ባሉት ጊዜ፤ የዳዊት ትምህርት ። 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ አድነኝ፤ በኀይልህም ፍረድልኝ። 2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማልኝ፤ የአፌንም ቃል አድምጥ። 3 ባዕዳን ተነሥተውብኛልና፤ ግፈኞች ነፍሴን ሽተዋታል፤ እግዚአብሔርንም ከምንም አልቈጠሩም። ሴላ 4 እነሆ፤ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፤ ጌታም ደግፎ ይይዘኛል። 5 የገዛ ክፋታቸው በሚያደቡብኝ ላይ ይመለስባቸው፤ በቃልህ ታማኝ ነህና አጥፋቸው። 6 በበጎ ፈቃድ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ነውና፣ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤ 7 ከመከራ ሁሉ ታድጎኛልና፤ ዐይኔም የጠላቶቼን ውድቀት ለማየት በቅቷል። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.