Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 118:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ፥ የጠላቶቼን ውድቀት አያለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ይረዳኝ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ነው፤ የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታ ሊረዳኝ ከጎኔ ነው፥ እኔም ጠላቶቼን በኩራት አያለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አቤቱ፥ የጽ​ድ​ቅ​ህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 118:7
10 Referencias Cruzadas  

አምላኬ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ በፊቴ ይሄዳል፤ ጌታዬ፥ ጠላቶቼን በንቀት ዐይን እንድመለከታቸው ያደርገኛል።


ነገር ግን አምላክ ረዳቴ ነው፤ ጌታም የሕይወቴ ደጋፊ ነው።


ከችግሬ ሁሉ አድነኸኛል፤ የጠላቶቼንም ውድቀት አየሁ።


እጅግ ከበዙ ጠላቶቼ ጋር ከማደርገው ጦርነት በሰላም ይመልሰኛል።


በእግዚአብሔር ያለው እምነት እጅግ የጸና ስለ ሆነ ከቶ አይፈራም፤ በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።


የጠላቶቼን መሸነፍ አየሁ፤ የአስጨናቂዎቼንም ውድቀት ሰማሁ።


የእግዚአብሔር መንፈስ የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በዐማሳይ ላይ ወረደ፤ እርሱም፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን! የእሴይ ልጅ ዳዊት ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን! ለአንተና አንተን ለሚረዱ ሁሉ ሰላም ይሁን! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይረዳሃል፤” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ዳዊትም እነርሱን በደስታ ተቀብሎ በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች አደረጋቸው።


መሥዋዕትህን በፍላጎቴ አቀርብልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ ተገቢ ስለ ሆነ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ


መከታችን እግዚአብሔር ሆይ! ወገኖቼ የአንተን ተበቃይነት እንዳይረሱ፥ አትግደላቸው፤ ነገር ግን በኀይልህ በትናቸው፤ አዋርዳቸውም።


‘አይዞህ አትፍራ፥ አትደንግጥ፥ ቀኝ እጅህን ይዤ እረዳሃለሁ’ እያልኩ የማበረታታህ፥ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios