መዝሙር 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ የእውነት አምላክ ነህ፤ እባክህን ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ! እኔ በጣም በጭንቀት ላይ ነበርኩ አንተ ግን ነጻ አወጣኸኝ፤ አሁንም ራራልኝና ጸሎቴን ስማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽድቄ አምላክ ሆይ፤ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤ ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤ ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ጽድቄን ሰማኝ፥ ከጭንቀቴም አሰፋልኝ፤ ይቅር አለኝ፥ ጸሎቴንም ሰማኝ። |
እርሱ በሚነግሥበት ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ ደኅንነት ያገኛል፤ የእስራኤልም ሕዝብ በሰላም ይኖራል፤ እርሱም ‘እግዚአብሔር ጽድቃችን’ ተብሎ ይጠራል።
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
ወንድሞች ሆይ! በእስያ ክፍለ ሀገር በነበርንበት ጊዜ የደረሰብንን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ ይህም የደረሰብን መከራ ልንሸከመው ከምንችለው በላይ ወድቆብን ስለ ነበር በሕይወት ለመኖር የነበረን ተስፋ እንኳ ተቋርጦ ነበር።
ከአንበሳና ድብ ያዳነኝ እግዚአብሔር ከዚህም ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም “መልካም ነው! እንግዲህ ሂድ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን!” ሲል መለሰለት።