12 ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ፤ በፊትህም ለዘለዓለም ታኖረኛለህ።
12 ስለ ጭንቀቴ ደግፈህ ይዘኸኛል፤ በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።
12 ጠላቴ እልል አይልብኝምና በዚህም በእኔ እንደ ተደሰትክ አወቅሁ።
እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን ይጠብቃል፤ እንደ ነገሥታትም በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ ለዘለዓለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።
የክፉዎች ኀይል ይሰበራል ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ያበረታቸዋል።
“አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸኝም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ።
ወደ አንተ እጠጋለሁ፤ ቀኝ እጅህም ቀና አድርጎ ይደግፈኛል።
እግዚአብሔር ወደ ጻድቃን ይመለከታል፤ ጸሎታቸውንም ያደምጣል።
አምላክ ሆይ! አንተን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቅንነትና ቀጥተኛነት እንዲጠብቁኝ አድርግ።
“ለመውደቅ ተቃርቤአለሁ” ባልኩ ጊዜ እግዚአብሔር ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደግፎ አቆመኝ።
እኔ በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ በምነቃበት ጊዜም የአንተን አምሳያ በማየቴ እደሰታለሁ።
የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ፊት ሙሉ ደስታ፥ በቀኝህም የዘለዓለም እርካታ ይገኛል።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም ፈወስከኝ።