ከዚህም የባሰ ራሴን አዋርዳለሁ፤ ለአንቺ እንደሚመስልሽ በዐይንሽ ፊት የተናቅሁ ብሆንም በእነርሱ ፊት ራስህን አዋረድክ ብለሽ በተናገርሽባቸው ልጃገረዶች ዘንድ እጅግ የተከበርኩ እሆናለሁ!”
መዝሙር 131:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤ ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤ ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤ ሐሳቤ ለዐጕል ትልቅነት አልተነሣሣም፤ ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት የዕርገት መዝሙር። አቤቱ፥ ልቤ አይታበይም፥ ዐይኖቼም ከፍ ከፍ አይሉም፥ ለትልልቅ ነገሮች፥ ከዐቅሜም በላይ ለሆኑት አልጨነቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ዳዊትን፥ ገርነቱንም ሁሉ ዐስብ፤ |
ከዚህም የባሰ ራሴን አዋርዳለሁ፤ ለአንቺ እንደሚመስልሽ በዐይንሽ ፊት የተናቅሁ ብሆንም በእነርሱ ፊት ራስህን አዋረድክ ብለሽ በተናገርሽባቸው ልጃገረዶች ዘንድ እጅግ የተከበርኩ እሆናለሁ!”
እኔ የማውቀው በጣም ትንሽ ሆኖ ሳለ ብዙ የምናገረው ለምን እንደ ሆነ ጠይቀሃል። በእርግጥ እኔ ስለማላውቃቸውና እጅግ ድንቅ ስለ ሆነ ነገር ተናግሬአለሁ።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ! በእነርሱ ላይ መቅሠፍትን እንድታመጣ ያሳሰብኩህ ጊዜ የለም፤ የመከራ ዘመን እንዲገጥማቸውም አልተመኘሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህንና የተናገርኩትን ሁሉ ታውቃለህ።
ታዲያ አንተ ለራስህ የተለየ መልካም ነገር እንዳደርግልህ ትፈልጋለህን? ይህን መፈለግ የለብህም፤ እኔ መቅሠፍትን በሰው ዘር ሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ ይሁን እንጂ በምትሄድበት ቦታ ሁሉ ሌላው ቢቀር ሕይወትህ እንድትተርፍ አደርጋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ራሳችሁን ከፍ ከማድረግ ይልቅ ትዕቢትን አስወግዳችሁ ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፤ በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።
ራሱንም ከወገኖቹ ከእስራኤላውያን እበልጣለሁ ብሎ እንዳይታበይና ከእግዚአብሔርም ትእዛዞች እንዳይርቅ ይጠብቀዋል። ይህን ቢያደርግ ለብዙ ዘመን ይነግሣል፤ ልጆቹም በእስራኤል ላይ ለብዙ ዘመን ይነግሣሉ።
በእናንተ በአማኞች መካከል በነበርንበት ጊዜ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ሕይወት እንደ ኖርን እናንተ ምስክሮች ናችሁ፤ እግዚአብሔርም ምስክር ነው፤
ሳሙኤልም በወይራ ዘይት የተሞላውን ቀንድ ወስዶ ዳዊትን በወንድሞቹ ፊት ቀባው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት አደረበት፤ ከዚያም ቀን ጀምሮ ከእርሱ አልተለየም፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ወደ ራማ ተመለሰ።
ከአገልጋዮቹም አንዱ “የቤተልሔም ከተማ ነዋሪ የሆነው እሴይ በገና መደርደር የሚችል ልጅ እንዳለው አይቼአለሁ ይህም ብቻ ሳይሆን ጀግና፥ መልከ ቀና፥ ብርቱ ወታደርና ንግግር ዐዋቂ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው” አለው።
ስለዚህ የሳኦል ባለሟሎች ይህን ጉዳይ ለዳዊት በምሥጢር ነገሩት፤ እርሱም፦ “እንደእኔ ላለ ዝቅተኛ ድኻ ሰው የንጉሥ ዐማች መሆን ቀላል ይመስላችኋልን?” አላቸው።