8 እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ከኃጢአታቸው ሁሉ ያድናቸዋል።
8 እርሱም እስራኤልን፣ ከኀጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።
8 እርሱም እስራኤልን ከበደሉ ሁሉ ያድነዋል።
“ሕዝቡን በምሕረት ስለ ጐበኘና ስላዳነ፥ የእስራኤል አምላክ፥ ጌታ ይመስገን!
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
አሁን እናንተ የምትኖሩት ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆነ ኃጢአት ሊገዛችሁ አይገባም።
እርስዋ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ስለሚያድን ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”
በደልህን እንደ ደመና ኃጢአትህን እንደ ማለዳ ጭጋግ አስወግጄአለሁ፤ ስለ አዳንኩህ ወደ እኔ ተመለስ።”
ሕጌን በመጣስ ከፈጸሙት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውንና በዐመፅ የፈጸሙትን ሥራ ሁሉ ይቅር እላለሁ።