ሰቈቃወ 2:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ሌሊቱን በሙሉ ተነሥታችሁ ጩኹ፤ በልባችሁ የሚሰማችሁን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ፊት አቅርቡ፤ በየመንገዱ ማእዘን በራብ ለሚዝለፈለፉ ልጆቻችሁ ሕይወት በጸሎት እጆቻችሁን ወደ እግዚአብሔር አንሡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሌሊቱ ሰዓት ሲጀምር፣ ተነሺ በሌሊት ጩኺ፤ በጌታ ፊት፣ ልብሽን እንደ ውሃ አፍስሺ፤ በየመንገዱ ዳር ላይ፣ በራብ ስለ ወደቁት፣ ስለ ልጆችሽ ሕይወት፣ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቆፍ። ተነሺ፤ በሌሊት በመጀመሪያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፤ በጎዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ። |
እኔ እፊት እፊት ሆኜ እየመራሁ ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄድ ነበር፤ በዓል የሚያደርጉት ሰዎችም በመዝሙርና በእልልታ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ በዚህ ዐይነት ያለፈውን ጊዜ ሳስታውስ ልቤ በሐዘን ይሰበራል።
ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።
ልጆችሽ በወጥመድ ውስጥ እንደ ተያዘ ድኩላ በየመንገዱ አደባባይ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤ በእነርሱም ላይ የአምላክሽ የእግዚአብሔር ተግሣጽና ቊጣ ወርዶባቸዋል።
ወደየመስኩ ብወጣ በጦርነት የተገደሉ ሰዎችን ሬሳ አያለሁ፤ ወደ ከተማም ብገባ በራብ ለመሞት የሚያጣጥሩ ሰዎችን አያለሁ፤ ነቢያትና ካህናት የራሳቸውን ጉዳይ ይከታተላሉ፤ ነገር ግን የሚያደርጉትን አያውቁም።”
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ ሴቶች፥ እግዚአብሔር የሚለውን አድምጡ፤ ቃሉንም ለመቀበል የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ እንዴት ማልቀስ እንደሚገባቸው ሴቶች ልጆቻችሁን አስተምሩ፤ ሙሾ የማውጣትንም ዘዴ ለወዳጆቻችሁ አስጠኑ።
በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም ያሉ ወላጆች በእርግጥ ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን ይበላሉ፤ በዚህ ዐይነት ሁላችሁንም እቀጣለሁ፤ የተረፉትንም በአራቱ ማእዘን እበትናቸዋለሁ።
እንደ ገዳይ ቀስት የሆነውን ራብ የማመጣባችሁ እንዲያጠፋችሁ ነው፤ ደጋግሜ ራብን አመጣባችኋለሁ፤ የምግብ አቅርቦታችሁም እንዲቋረጥ አደርጋለሁ።
እናንተ የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ልጆቻችሁ ተማርከው ስለሚወሰዱ፥ ስለ ነዚህ ስለምትወዱአቸው ልጆቻችሁ ሐዘን ጠጒራችሁን ተላጩ፤ ራሳችሁም እንደ ጥንብ አንሣ ራስ መላጣ ይሁን።
ይህም ሁሉ ሆኖ የቴብስ ከተማ በጠላት ተይዛ ሕዝቦችዋ ተማርከዋል፤ ሕፃናትዋም በድንጋይ ተፈጥፍጠው በየመንገዱ ወድቀዋል፤ በልዑላኑ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ሹማምንቱንም በሰንሰለት አሰሩአቸው።
ስለዚህ የቤቱ ጌታ የሚመጣበትን ጊዜ አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ምናልባትም ወደ ማታ፥ ወይም በእኩለ ሌሊት፥ ወይም ዶሮ ሲጮኽ፥ ወይም ጠዋት በማለዳ ይመጣ ይሆናል፤
ከእኩለሌሊት ጥቂት ቀደም ብሎ፥ ዘብ ጠባቂዎች ከተቀያየሩ በኋላ ጌዴዎንና ከእርሱ ጋር የተመደቡት መቶ ሰዎች ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ እምቢልታዎቻቸውን ነፉ፤ የያዙትንም ማሰሮ ሁሉ ሰባበሩ።
እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፦ “አይደለም ጌታዬ ሆይ! እኔ በጥልቅ ሐዘን ላይ ያለሁ ሰው ነኝ፤ ወይን ጠጅም ሆነ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም፤ ነገር ግን ችግሬን ለእግዚአብሔር እያቀረብኩ ነው።
እነርሱም በአንድነት በምጽጳ ተሰበሰቡ፤ ውሃም ቀድተው ለእግዚአብሔር መባ አድርገው በማፍሰስ በዚያን ዕለት ቀኑን ሙሉ ጾሙ፤ “እኛ እግዚአብሔርን በድለናል” ብለውም ተናዘዙ፤ ሳሙኤል በእስራኤላውያን መካከል ይፈርድ የነበረው በምጽጳ ነበር።