Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሰቈቃወ 2:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የሌሊቱ ሰዓት ሲጀምር፣ ተነሺ በሌሊት ጩኺ፤ በጌታ ፊት፣ ልብሽን እንደ ውሃ አፍስሺ፤ በየመንገዱ ዳር ላይ፣ በራብ ስለ ወደቁት፣ ስለ ልጆችሽ ሕይወት፣ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እናንተ ሌሊቱን በሙሉ ተነሥታችሁ ጩኹ፤ በልባችሁ የሚሰማችሁን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ፊት አቅርቡ፤ በየመንገዱ ማእዘን በራብ ለሚዝለፈለፉ ልጆቻችሁ ሕይወት በጸሎት እጆቻችሁን ወደ እግዚአብሔር አንሡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ቆፍ። ተነሺ፤ በሌ​ሊት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌ​ታም ፊት ልብ​ሽን እንደ ውኃ አፍ​ስሺ፤ በጎ​ዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃ​ና​ትሽ ነፍስ እጆ​ች​ሽን ወደ እርሱ አንሺ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 2:19
31 Referencias Cruzadas  

መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፥ ጠንካራ ዓለቴና መጠለያዬ እግዚአብሔር ነው።


ፍርድህን በምድር ላይ በፈረድክ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።


በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥ በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ለመንሁ።


ማለዳም ገና ጎሕ ሳይቀድ፥ ኢየሱስ ተነሥቶ ከቤት ወጣ፤ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራም ሄዶ ይጸልይ ጀመር።


ሐናም እንዲህ ብላ መለሰችለት፥ “ጌታዬ ሆይ፤ አይደለም፤ እኔስ ልቧ ክፉኛ ያዘነባት ሴት ነኝ፤ የልቤን ኀዘን በጌታ ፊት አፈሰስሁ እንጂ፥ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም።


ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን፥ እጆቼን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ይሁን።


ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፥ ጌዴዎንና አብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮች ሰበሩ።


በፏፏቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች፥ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።


በነዚህም ወራት ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱንም በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።


እንግዲህ የቤቱ ባለቤት በምሽት ወይም በውድቅት፥ በዶሮ ጩኸት ወይም ጎሕ ሲቀድ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤


ከሌሊቱም በአራተኛው ክፍል ኢየሱስ በባሕር ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ።


አቤቱ፥ በሌሊት ስምህን አሰብሁ፥ ሕግህንም ጠበቅሁ።


ወደ መቅደስህ ማደሪያ እጄን ባነሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።


ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ በየአደባባዩ ራስ ላይ ተኝተዋል፤ በጌታ ቁጣና በአምላክሽ ተግሣጽ ተሞልተዋል።


እንግዲህ በሁሉ ስፍራ ያሉ ወንዶች ንዴትንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሡ እንዲጸልዩ ፈቃዴ ነው።


የሚገድሉና የሚያጠፉ የራብ ፍላፃ በወረወርሁ ጊዜ፥ እንዳጠፋችሁ እወረውራቸዋለሁ፥ በእናንተ ላይ ረሃብን እጨምርባችኋለሁ፥ የምግባችሁንም በትር እሰብራለሁ።


ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፥ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፥ ፍርድንም አደርግብሻለሁ፥ ከአንቺም የተረፉትንም ሁሉ ወደ ሁሉም ነፋሳት እበትናለሁ።


በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ ጌታንም ባርኩ።


ቸርነትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።


ከእንጀራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ጩኸቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል።


እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ውሃ ቀድተው በጌታ ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለትም ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።


ሆኖም ግን ተማርካ ተወሰደች፤ ሕፃናቶችዋ በመንገዶች ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፤ በከበርቴዎችዋ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።


ነፍሴ እግዚአብሔርን፥ ሕያው አምላክን ተጠማች፥ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?


ዘወትር፦ አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።


ሮሮዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፥ መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ።


እናንተ ሴቶች ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ ጆሮአችሁም የአፉን ቃል ትቀበል፥ ለሴቶች ልጆቻችሁም ልቅሶውን፥ እያንዳንዳችሁም ለባልንጀሮቻችሁ ዋይታውን አስተምሩ።


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ ደዌ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቁት አገር ሄደዋልና።’”


ደስ ስለምትሰኚባቸው ልጆች ራስሽን ንጪ፥ ፀጉርሽንም ተቆረጪ፤ መላጣነትሽን እንደ ንስር አስፊ፤ በምርኮ ከአንቺ ተወስደዋልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios