Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማርቆስ 13:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ስለዚህ የቤቱ ጌታ የሚመጣበትን ጊዜ አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ምናልባትም ወደ ማታ፥ ወይም በእኩለ ሌሊት፥ ወይም ዶሮ ሲጮኽ፥ ወይም ጠዋት በማለዳ ይመጣ ይሆናል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 “እንግዲህ የቤቱ ባለቤት በምሽት ወይም በውድቅት፣ በዶሮ ጩኸት ወይም ጎሕ ሲቀድድ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 እንግዲህ የቤቱ ባለቤት በምሽት ወይም በውድቅት፥ በዶሮ ጩኸት ወይም ጎሕ ሲቀድ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 13:35
8 Referencias Cruzadas  

ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት በኋላ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየተራመደ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጣ።


እንግዲህ ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ።


ነገር ግን ይህን ዕወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ሰዓት ሌባ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ ነቅቶ በጠበቀ ነበር፤ ቤቱም እንዲቆፈር ባልተወም ነበር።


እንዲሁም የሰው ልጅ በማታስቡት ሰዓት ስለሚመጣ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ።”


ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ።


“ለእናንተ እንደ ነገርኳችሁ ለሌሎችም ሁሉ ትጉ! እላለሁ።”


ኢየሱስም “በእውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት አንተ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው።


ደቀ መዛሙርቱ ከወደፊታቸው በሚነፍሰው ነፋስ ምክንያት መቅዘፍ ተቸግረው ሲጨነቁ አያቸው፤ ከሌሊቱም ከዘጠኝ እስከ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ፤ አልፎአቸውም ሊሄድ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos