ኢያሱ 17:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ የዮሴፍ በኲር ልጅ የነበረው የምናሴ ነገድ ድርሻ የሚከተለው ነው። የምናሴ በኲር ልጅ የገለዓድ አባት ማኪር የጦር ጀግና ስለ ነበረ ገለዓድና ባሳን በርስትነት ተሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናሴ የዮሴፍ የበኵር ልጅ እንደ መሆኑ መጠን፣ ለነገዱ የተመደበለት ድርሻ ይህ ነበር፤ የምናሴ የበኵር ልጅ ማኪር፣ የገለዓዳውያን አባት ብርቱ ጦረኛ ስለ ነበር ገለዓድና ባሳን ድርሻው ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለምናሴ ነገድ ዕጣው ይህ ነው፤ የዮሴፍ በኩር እርሱ ነውና። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴ ልጆች ነገድ ድንበር ይህ ነው፤ የዮሴፍ በኵር እርሱ ነውና። የምናሴም በኵር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምናሴ ነገድ ዕጣ ይህ ነው፥ የዮሴፍ በኩር እርሱ ነውና። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ሰልፈኛ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ። |
ዮሴፍ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ማድረጉን ባየ ጊዜ ቅር ተሰኘ፤ ስለዚህ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤
በዚያም አበኔር ኢያቡስቴን በገለዓድ ግዛቶች፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም ይኸውም በመላው እስራኤል ላይ እንዲነግሥ አደረገ።
ነገር ግን የገሹርና የአራም ነገሥታት ሥልሳ የሚያኽሉ ታናናሽ ከተሞችን ከዚያው ከገለዓድ ድል አድርጎ ያዘ፤ ይህም የያኢርንና የቀናትን መንደሮች እንዲሁም በአቅራቢያቸው ያሉትንም ታናናሽ ከተሞች የሚያጠቃልል ነበር፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ናቸው፤
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ በርስትነት የምታካፍላቸው የመሬት ድንበር የሚከተለው ነው፤ የዮሴፍ ነገድ ሁለት ድርሻ ይኖረዋል።
የሔፌር፥ የገለዓድ፥ የማኪር፥ የምናሴ፥ የዮሴፍ ልጅ የሆነው ጸሎፍሐድ፥ ማሕላ፥ ኖዓ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ቲርጻ ተብለው የሚጠሩ ሴቶች ልጆች ነበሩት።
ስለዚህ ሙሴ የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንንና የባሳንን ንጉሥ የዖግን ግዛት በዙሪያቸው ያሉትን ከተሞችና አገሮች ጭምር ለጋድና ለሮቤል ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠ፤
ከማያፈቅራት ሚስቱ የተወለደ ቢሆንም እንኳ ለበኲር ልጁ የሚሰጠው ድርሻ ከሌሎቹ የነፍስ ወከፍ ድርሻ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን አለበት፤ ስለዚህም ያ ሰው ልጁ በመጀመሪያ በመወለዱ በኲር መሆኑን ተረድቶ የብኲርና ድርሻውን ሊሰጠው ይገባል።
ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ያለው ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች በየወገናቸው ተሰጠ፤ እነርሱም አቢዔዜር፥ ሔሌቅ፥ አሥሪኤል፥ ሼኬም፥ ሔፌርና ሸሚዳዕ የተባሉት ናቸው፤ የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ዘሮች በየወገናቸው የሚከተሉት ናቸው።
ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሙሴ ርስት በባሳን ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለእኩሌቶቹ ደግሞ በዮርዳኖስ ምዕራብ በኩል ከወንድሞቻቸው ጋር ኢያሱ መሬት ሰጣቸው፤ ኢያሱም ባሰናበታቸው ጊዜ ባረካቸው፤
ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።