Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 32:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ስለዚህ ሙሴ የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንንና የባሳንን ንጉሥ የዖግን ግዛት በዙሪያቸው ያሉትን ከተሞችና አገሮች ጭምር ለጋድና ለሮቤል ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ከዚያም ሙሴ፣ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛትና የባሳንን ንጉሥ የዐግን ግዛት፣ ማለትም ምድሪቱንና ከነከተሞቿ በዙሪያዋ ያለውን ግዛት በሙሉ ለጋድና ለሮቤል ነገዶች እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ግዛት፥ ምድሪቱንና ከተሞቹን በከተሞቹም ዙሪያ ያሉትን ግዛቶች ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ሙሴም ለጋድ ልጆ​ችና ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለዮ​ሴ​ፍም ልጅ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን መን​ግ​ሥት፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን መን​ግ​ሥት፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም፥ ከተ​ራ​ሮ​ችም ጋር ከተ​ሞ​ችን፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ​ትን የም​ድ​ሪ​ቱን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ግዛት፥ ምድሪቱንና በዙሪያዋ ያሉትን ከተሞች ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 32:33
21 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ዳዊት ከእነዚያ ዘመዶች መካከል ምርጥ የሆኑ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ የቤተሰብ አለቆችን መረጠ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ማለትም በሮቤል፥ በጋድና በምናሴ ነገድ እኩሌታ ግዛቶች መንፈሳዊውንና ዓለማዊውን ጉዳይ ሁሉ የማስተዳደር ኀላፊነት ሰጣቸው።


የሮቤል፥ የጋድና በስተ ምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ በጋሻና በሰይፍ እንዲሁም በቀስት ውጊያ በደንብ የሠለጠኑ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሥልሳ ወታደሮች ነበሩአቸው፤


የሮቤልና የጋድ ነገዶች እጅግ ብዙ የከብት መንጋ ነበራቸው፤ የያዕዜርና የገለዓድ ምድር ለከብት ተስማሚ መሆኑን ባዩ ጊዜ፥


በእርሱም መሪነት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፤ በዚህ በዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን የርስት ድርሻችንን ለራሳችን ለማስቀረት ወደ ጦርነት እንሄዳለን።”


የሮቤልና የጋድ ነገዶች፥ እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ በየቤተሰባቸው በመከፋፈል፥


በዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ፥ በፀሐይ መውጫ በኩል ርስታቸውን ተቀብለዋል።”


ምድራቸውንም ወርሰን ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለእኩሌታ የምናሴ ነገድ ርስት እንዲሆን አከፋፍለን ሰጥተናል፤


እስራኤላውያን ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ አራባ ሁሉ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ በኩል አሸንፈው ምድራቸውን የያዙባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤


እንግዲህ እነዚህ ሁለት ነገሥታት በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴና በእስራኤል ሕዝብ ጦርነት ድል ሆነው ነበር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም ይህን ምድር ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው።


ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን ምድር ለሁለት ተኩል ነገዶች ርስት አድርጎ ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለሌዋውያን ግን በእነርሱ መካከል ርስት አልሰጣቸውም።


እነሆ አሁን አምላካችሁ እግዚአብሔር በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለወገኖቻችሁ ለእስራኤላውያን ሰላምን ሰጥቶአቸዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ወደ ሰጣችሁ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ወደሚገኘውና ርስት አድርጋችሁ ወደ ወረሳችሁት ምድር ተመልሳችሁ ሂዱ፤


ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሙሴ ርስት በባሳን ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለእኩሌቶቹ ደግሞ በዮርዳኖስ ምዕራብ በኩል ከወንድሞቻቸው ጋር ኢያሱ መሬት ሰጣቸው፤ ኢያሱም ባሰናበታቸው ጊዜ ባረካቸው፤


ከዕብራውያን መካከል አንዳንዶቹ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ግዛቶች ሄዱ። ሳኦል ግን እስከዚህ ጊዜ ድረስ በጌልገላ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበረው ሠራዊት ከፍርሃት የተነሣ ይንቀጠቀጥ ነበር፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos