Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 50:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የኤፍሬምንም ልጆችና የልጅ ልጆች እስከሚያይ ድረስ ቈየ፤ ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች እንደ ልጆቹ አድርጎ ተቀበላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ አየ። የምናሴ ልጅ ማኪር የወለዳቸውም ልጆች በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የኤፍሬምንም ልጆችና የልጅ ልጆች እስከሚያይ ድረስ ቈየ፤ ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች እንደ ልጆቹ አድርጎ ተቀበላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ዮሴ​ፍም የኤ​ፍ​ሬ​ምን ልጆች እስከ ሦስት ትው​ልድ አየ። የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጆ​ችም በዮ​ሴፍ ጭን ላይ ተወ​ለዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ዮሴፍም የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ አየ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጆችም በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 50:23
11 Referencias Cruzadas  

እርስዋም “እነሆ፥ አገልጋዬ ባላ እዚህ አለች፤ በእኔ ምትክ ልጅ እንድትወልድልኝ ወደ እርስዋ ግባ፤ በዚህ ዐይነት በእርስዋ አማካይነት የልጆች እናት እሆናለሁ” አለችው።


አባቱ ግን “ዐውቄአለሁ፤ ልጄ ዐውቄአለሁ፤ የምናሴም ዘር ታላቅ ሕዝብ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የእርሱ ታናሽ ወንድም ከእርሱ ይበልጥ ታላቅ ይሆናል፤ ዘሮቹም ታላላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” አለ።


ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ ይልቅ ይቀላሉ፤ ጥርሶቹ ከወተት ይልቅ ይነጣሉ።


ዮሴፍ ከአባቱ ቤተሰቦች ጋር በግብጽ ተቀመጠ፤ ከዚያም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት እስኪሆነው ኖረ፤


ምናሴ ከሶርያዊት ቊባቱ አስሪኤልና ማኪር ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤


ከዚህም በኋላ ኢዮብ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ ለማየት በቃ።


የልጆችህን ልጆች ለማየት እንድትበቃ ያድርግህ! ሰላም ከእስራኤል ጋር ይሁን!


የሸመገሉ ሰዎች በልጅ ልጆቻቸው እንደሚመኩ ልጆችም በአባቶቻቸው ይመካሉ።


ስለዚህ ሙሴ የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንንና የባሳንን ንጉሥ የዖግን ግዛት በዙሪያቸው ያሉትን ከተሞችና አገሮች ጭምር ለጋድና ለሮቤል ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠ፤


የምናሴ ልጅ የማኪር ቤተሰብ የገለዓድን ምድር በመውረር ወረሰ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንን አባረረ።


ይህ የዮሴፍ በኲር ልጅ የነበረው የምናሴ ነገድ ድርሻ የሚከተለው ነው። የምናሴ በኲር ልጅ የገለዓድ አባት ማኪር የጦር ጀግና ስለ ነበረ ገለዓድና ባሳን በርስትነት ተሰጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos