አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።
ዮሐንስ 14:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። |
አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።
ጲላጦስም “ታዲያ፥ አንተ ንጉሥ ነኻ?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንኩ አንተ ትላለህ፤ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ልመሰክር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማል” ሲል መለሰ።
ከሰማይ የወረደው ሕይወትን የሚሰጥ እንጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ሁሉ ለዘለዓለም ይኖራል፤ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን እኔ የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።”
ስለዚህ መዳን ከእርሱ በቀር በሌላ በማንም የለም፤ እኛ ልንድንበት የሚገባን እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ስም ከእርሱ በቀር በመላው ዓለም ማንም የለም።”
የጌታንም መንገድ የሚከተሉትን ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ሲያገኝ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት የሚያስችል ደብዳቤ ለደማስቆ ምኵራቦች ተጽፎ እንዲሰጠው ሊቀ ካህናቱን ጠየቀ።
ይህም ጸጋ የተሰጠኝ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለአሕዛብ በማብሠር እንደ ካህን ሆኜ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል ነው፤ ስለዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰና እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ አገለግላለሁ።
ወደዚህ አሁን በእምነት ጸንተን ወደምንገኝበት ጸጋ የገባነው በእርሱ ስለ ሆነ በተስፋ የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች በመሆናችን እንመካለን።
ይህም የሆነው በሞት ምክንያት ኃጢአት እንደ ነገሠ ሁሉ እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲገኝ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን በመስጠት ይነግሣል።
ስለዚህ እነርሱን ለማማለድ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእርሱ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ በፍጹም ሊያድናቸው ይችላል።
የመጀመሪያይቱ ድንኳን እስካለች ድረስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚወስደው መንገድ ገና ያልተገለጠ መሆኑን መንፈስ ቅዱስ በዚህ ዐይነት ያሳያል።
እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።
ስለዚህ ሕያው ድንጋይ ወደ ሆነው ወደ ጌታ ኢየሱስ ቅረቡ፤ ይህ ድንጋይ ሰዎች ንቀው የተዉት፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የተመረጠና ክቡር ዋጋ ያለው ነው።
ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።
የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።
ጥምቀቱን በሚያመለክት ውሃና ሞቱን በሚያመለክት ደም የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ የመጣው በውሃ ብቻ ሳይሆን በውሃና በደም ነው። ይህም እውነት ስለ ሆነ ይህ ነገር እውነት መሆኑን መንፈስ ቅዱስ ይመሰክራል፤
በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የማይኖርና ከእርሱም ርቆ የሚሄድ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የለም፤ በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የሚኖር ሰው ግን አብና ወልድ ከእርሱ ጋር አሉ።
ከዚህ በኋላ ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ፥ ነጭ ፈረስም አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ታማኝና እውነተኛ የሚባል ነው፤ እርሱ በትክክል ይፈርዳል፤ ይዋጋልም፤
መንፈስ ቅዱስና ሙሽራይቱ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም “ና!” ይበል፤ የተጠማም ይምጣ፤ የፈለገም የሕይወትን ውሃ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ ይጠጣ።
“ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ፥ አሜን ከሆነው፥ ታማኝና እውነተኛ ምስክር ከሆነው፥ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መገኛ ከሆነው የተነገረ ነው፤
“ለፊላደልፍያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ቅዱስና እውነተኛ ከሆነው፥ የዳዊት ቤት ቊልፍ ከያዘው የተነገረ ነው፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋውም፤ እርሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍተውም።