ኤርምያስ 6:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርሻ አትውጡ፤ በመንገድ ላይም አትዘዋወሩ፤ በየአቅጣጫው ሽብር ስለ ሆነ ከጠላት ሰይፍ ተጠንቀቁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላት ሰይፍ ታጥቋል፤ በየቦታውም ሽብር ሞልቷል፤ ስለዚህ ወደ ውጭ አትውጡ፤ በየመንገዱ አትዘዋወሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠላት ሰይፍና ድንጋጤ ከብበዋችኋልና ወደ ሜዳ አትውጡ በመንገድም ላይ አትሂዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠላት ሰይፍ ከብበዋችኋልና ወደ ሜዳ አትውጡ፤ በመንገድም ላይ አትሂዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠላት ሰይፍና ድንጋጤ ከብበዋችኋልና ወደ ሜዳ አትውጡ በመንገድም ላይ አትሂዱ። |
ወደየመስኩ ብወጣ በጦርነት የተገደሉ ሰዎችን ሬሳ አያለሁ፤ ወደ ከተማም ብገባ በራብ ለመሞት የሚያጣጥሩ ሰዎችን አያለሁ፤ ነቢያትና ካህናት የራሳቸውን ጉዳይ ይከታተላሉ፤ ነገር ግን የሚያደርጉትን አያውቁም።”
ብዙ ሰዎች ፈርተው በሹክሹክታ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፤ “አሁን ኤርምያስን ለመክሰስ መልካም አጋጣሚ ነው!” ወዳጆቼ ናቸው የሚባሉት እንኳ ስሕተት እንዳደርግ ይጠባበቃሉ፤ “ኤርምያስ ሊታለል ይችል ይሆናል፤ ይህም ከሆነ እርሱን ይዘን እንበቀለዋለን፤” ይላሉ።
እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ማታለል አይሆንብህምን? ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለሃቸው ነበር፤ እነሆ አሁን ሰይፍ በአንገታቸው ላይ ተቃጥቶአል” አልኩ።
በምድሪቱ ሁሉ ላይ መለከት ንፉ! ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ወደተመሸጉ ከተሞች እንዲሸሹ ንገሩአቸው።
“ነገር ግን ይህ የማየው ነገር ምንድን ነው? ከፍርሃት የተነሣ ወደ ኋላ በመመለስ ላይ ናቸው፤ ወታደሮቻቸው ድል ሆኑ፤ በየአቅጣጫው ፍርሀትና ሽብር ስላለ ወደ ኋላ መለስ ብለው ሳያዩም ወደ ፊት ሸሹ።
ድንኳኖቻቸውን፥ መንጋዎቻቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ውሰዱ፤ ግመሎቻቸውን ለራሳችሁ ውሰዱ። ‘በዙሪያው ሽብር ተነሥቷል’ ብለው ይጮኻሉ።”
እኔ ከሁሉም አቅጣጫ ሽብር አመጣባችኋለሁ፤ ሁላችሁም ትሸሻላችሁ፤ ሁሉም ወደፊቱ ሸሽቶ ስለሚበታተን የሸሹትን ስደተኞች የሚሰበስብ አይገኝም።
የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ዝም ብለን መቀመጣችን ለምንድን ነው? አምላካችን እግዚአብሔር ሞት ፈርዶብናል፤ እርሱን ስለ በደልን የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ አድርጎናል። ኑ! ወደተመሸጉ ከተሞች ሮጠን እዚያ እንሙት፤
የበዓል ቀን ይመስል ጠላቶቼን ከየቦታው ጋብዘሃል፤ በቊጣህ ቀን አንድም ያመለጠ ወይም በሕይወት የተረፈ የለም፤ ወልጄ ያሳደግኋቸውን ጠላቴ ፈጃቸው።