በማግስቱ ታላቂቱ ልጅ እኅቷን “ትናንት ማታ እኔ ከእርሱ ጋር ተኝቼአለሁ፤ ዛሬም እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተን እናስክረውና አንቺም አብረሽው ተኚ፤ በዚህ ዐይነት ሁለታችንም ከአባታችን ልጆች ወልደን ዘራችን እንዳይጠፋ እናድርግ” አለቻት።
ኤርምያስ 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን? አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩ በንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸውማል ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፥ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፥ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ። |
በማግስቱ ታላቂቱ ልጅ እኅቷን “ትናንት ማታ እኔ ከእርሱ ጋር ተኝቼአለሁ፤ ዛሬም እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተን እናስክረውና አንቺም አብረሽው ተኚ፤ በዚህ ዐይነት ሁለታችንም ከአባታችን ልጆች ወልደን ዘራችን እንዳይጠፋ እናድርግ” አለቻት።
ይህም ሁሉ ሆኖ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ከሚያደርገው ክፉ ነገር ሁሉ አልተመለሰም፤ ይልቁንም እርሱ በሠራቸው መሠዊያዎች የሚያገለግሉ ከሌዊ ዘር ውጪ ከሆኑ ቤተሰቦች መምረጡን ቀጥሎ ካህን ለመሆን ከፈለገ ማንኛውንም ሰው ይሾመው ነበር፤
ንጉሡም ለሦስተኛ ጊዜ ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሌላ መኰንን ላከ፤ ይህኛው መኰንን ግን ወደ ኰረብታው በመውጣት በኤልያስ ፊት በጒልበቱ ተንበርክኮ እንዲህ ሲል ለመነ፤ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት ሰዎች ምሕረት አድርግልን! ሕይወታችንንም ከሞት አድን!
እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”
እንዲሁም “ተደብድቤአለሁ፤ ነገር ግን አልተጐዳሁም፤ ተመትቼአለሁ፤ ሕመሙ ግን አልተሰማኝም፤ መቼ ነው የምነቃው? ሌላ ተጨማሪ መጠጥ የምጠጣው መቼ ይሆን?” ትላለህ።
አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።
ስለዚህ የቊጣውን ግለትና አስፈሪውን ጦርነት በላያችን ላይ አወረደ፤ በዙሪያችን እሳት አቀጣጠለ፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ አልተረዳነውም፤ አቃጠለን ልብም አላደረግነውም።
ገለባ በነፋስ እንደሚበተን፥ በምድሪቱ ውስጥ ባሉት ከተሞች ሁሉ በተንኳችሁ፤ ከክፉ ሥራችሁም ካለመመለሳችሁ የተነሣ፥ እናንተን ሕዝቤን አጠፋኋችሁ፤ ልጆቻችሁ ሁሉ እንዲገደሉ አደረግሁ።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነርሱ እልኸኞች ሆነው ለቃሌ ስላልታዘዙ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ በሚገኙ ስፍራዎች ሁሉ ይመጣል ብዬ ያስታወቅኹትን መቅሠፍት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ።”
የበልጉም ሆነ የክረምት ዝናብ ሊቀር የቻለው በዚህ ምክንያት ነው፤ አንቺ ዐይነ ዐፋርነትን አስወግደሽ እንደ አመንዝራ ሴት ኀፍረተቢስ ሆነሻል።
ዓላማህ ታላቅ ነው፤ ሥራህም ኀያል ነው፤ ሕዝቦች የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ ታያለህ፤ ለእያንዳንዱም ሰው እንደአካሄዱና እንደየሥራው ዋጋውን ትከፍላለህ።
ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ራሳችሁን ዝቅ በማድረግ ትሑታን ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ ለእኔ ክብር አልሰጣችሁኝም፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተ በሰጠሁትም ሕግና ደንብ ጸንታችሁ መኖር አልፈለጋችሁም።
ይህ ሕዝብ ለእኔ ለአምላኩ የማይታዘዝና ከቅጣቱም ሥነ ሥርዓትን መማር የማይፈልግ ሆኖአል፤ በዚህ ምክንያት እውነት ጨርሳ ጠፍታለች፤ ስለ እርስዋ በአንደበቱ የሚያነሣ እንኳ የለም።”
ኢየሩሳሌም ሆይ! ሴሰኛነትሽ አርክሶሻል፤ እኔ እንኳ ላነጻሽ ብፈቅድ አንቺ ከርኲሰትሽ አልነጻሽም። የቊጣዬ ኀይል እስከሚገለጥብሽ ድረስ ዳግመኛ ንጹሕ አትሆኚም።
በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ አመጣህ፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ከኃጢአታችን በመመለስና እውነትን በመከተል የአንተን ምሕረት ለማግኘት ወደ አንተ አልጸለይንም።
“በግብጽ ምድር የላክሁትን ዐይነት መቅሠፍት ላክሁባችሁ፤ ጐልማሶቻችሁ በሰይፍ እንዲሞቱ፥ ፈረሶቻችሁም እንዲማረኩ አደረግሁ፤ በሰፈራችሁ በሞቱ ሰዎች የበድን ግማት አፍንጫችሁን ሞላሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ደመሰስኩ ከእናንተም ብዙዎችን ደመሰስኩ፤ እናንተም የተረፋችሁት በእሳት ከተቀጣጠለ በኋላ ተነጥቆ እንደ ወጣ እንጨት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
ሰዎች ውሃ መጠጣት ፈልገው ከከተማ ወደ ከተማ ሄዱ፤ ነገር ግን በቂ ውሃ ባለማግኘታቸው ጠጥተው ሊረኩ አልቻሉም፤ እናንተም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
“ሰብላችሁን የሚያደርቅ ብርቱ ነፋስ ላክሁባችሁ፤ አትክልታችሁንና የወይን ተክላችሁን የበለስና የወይራ ዛፋችሁን ሁሉ አንበጣ በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
እኔም ይህን ሁሉ በማድረጌ ‘ሕዝቤ ያከብረኛል፤ ተግሣጼንም ይቀበላል፤ የደረሰበትንም ተግሣጽ ሁሉ አይረሳም’ ብዬ ነበር፤ ሕዝቤ ግን እየባሰበት ሄደ፤ በክፉ ሥራውም ረከሰ።”
ከዚህም በቀር እኛ ሁላችን የሚቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ፥ በሕይወት ለመኖር ለመንፈሳዊ አባታችን በይበልጥ መታዘዝ እንዴት አይገባንም!