Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 4:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ሰዶምንና ገሞራን እንደ ደመሰስኩ ከእናንተም ብዙዎችን ደመሰስኩ፤ እናንተም የተረፋችሁት በእሳት ከተቀጣጠለ በኋላ ተነጥቆ እንደ ወጣ እንጨት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣ አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ እንዲሁ ገለባበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን አስ​ቀ​ድሜ እንደ ገለ​በ​ጥ​ኋ​ቸው፥ እን​ዲሁ ገለ​በ​ጥ​ኋ​ችሁ፤ እና​ን​ተም ከእ​ሳት ውስጥ እንደ ተነ​ጠቀ ትን​ታግ ሆና​ችሁ፤ በዚ​ህም ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፥ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 4:11
24 Referencias Cruzadas  

የባቢሎን መንግሥት ከመንግሥታት ሁሉ እጅግ የተዋበች ናት፤ ለሕዝብዋም መመኪያ ናት፤ ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር ባቢሎንን እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ እገለብጣታለሁ!


ረጋ እንዲል፤ እንዳይፈራ፥ በእሳት ተቀጣጥሎ እንደሚነድ እንደ ግንድ ጢስ በሆኑት በሬዚንና በሶርያው በሬማልያ ልጅ ምክንያት እንዳይሸበር ንገረው።


እርሱ ከምሥራቅ ሶርያውያንን፥ ከምዕራብ ፍልስጥኤማውያንን ልኮ እስራኤልን እንዲወሩ አደረገ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ቊጣው አልበረደም፤ ስለዚህ እጁ እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተቃጣ ነው።


ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚገኙ ነቢያትም ከዚህ የባሰ ክፋት ሲያደርጉ አይቼአለሁ፤ እነርሱ ያመነዝራሉ፤ ሐሰትም ይናገራሉ፤ ሰዎችን ለክፉ ሥራ ያነሣሣሉ፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ ከክፉ ሥራቸው አይመለሱም። ስለዚህ እነርሱ በእኔ ዘንድ እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ሕዝብ የከፉ ናቸው።


ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ከሚገኙ ከተሞች ጋር በተደመሰሱ ጊዜ የደረሰባቸው ጥፋት እንዲሁ በተመሳሳይ በኤዶምም ላይ ይደርሳል። ዳግመኛም በዚያ ሰፍሮ የሚኖር ከቶ አይገኝም።


እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።


ሰዶምንና ገሞራን በአካባቢያቸው ካሉ ከተሞች ጋር በደመሰስኩ ጊዜ እንደሆነው እንዲሁም በባቢሎን ማንም እንደገና ሰፍሮ መኖር አይችልም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ኢየሩሳሌም ሆይ! ሴሰኛነትሽ አርክሶሻል፤ እኔ እንኳ ላነጻሽ ብፈቅድ አንቺ ከርኲሰትሽ አልነጻሽም። የቊጣዬ ኀይል እስከሚገለጥብሽ ድረስ ዳግመኛ ንጹሕ አትሆኚም።


“እነርሱ ግን ወደ እኔ መመለስን እምቢ ስላሉ ወደ ግብጽ ይመለሳሉ፤ ለአሦርም ንጉሥ ተገዥዎች ይሆናሉ።


“እስራኤል ሆይ! እንዴት እተውሃለሁ? እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? በአዳማና በጸቦይም ያደረግኹትንስ፥ እንዴት አደርግብሃለሁ? ለአንተ ያለኝ ፍቅር ታላቅ ስለ ሆነ፥ ይህን ሁሉ ላደርግብህ አልፈቅድም!


“በአፋችሁ የምትቀምሱት እህል አሳጥቼ በከተሞቻችሁ ሁሉ ችጋር ለቅቄባችኋለሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።


እናንተንና የሥራችሁን ውጤት ሁሉ በዋግ፥ በሌላም በተክሎች በሽታና በበረዶ መታሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ግን በንስሓ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።


የእግዚአብሔርም መልአክ ሰይጣንን “አንተ ሰይጣን! እግዚአብሔር ይገሥጽህ! ኢየሩሳሌምን የሚወድ እግዚአብሔር ይገሥጽህ! ይህ ሰው እኮ ከእሳት ውስጥ ተርፎ እንደ ወጣ እንጨት ነው” አለው።


እንዲሁም ኢሳይያስ “የሠራዊት ጌታ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ የሰዶምና የገሞራ ከተሞች እንደ ጠፉ እኛም በጠፋን ነበር” ሲል አስቀድሞ ተናግሮአል።


ሥራው በእሳት ተቃጥሎ የተደመሰሰበት ግንበኛ ግን ዋጋው ይቀርበታል፤ ይሁን እንጂ እርሱ ራሱ፥ በእሳት ውስጥ አልፎ ሳይቃጠል እንደሚቀር ሰው ይድናል።


በዝናብ ፈንታ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር በአንተ ላይ በዐውሎ ነፋስ የሚነዳ ትቢያና አሸዋ ይልክብሃል።


ምድሪቱም ሁሉ በዲንና በጨው ትሸፈናለች፤ ምንም ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አታበቅልም፤ እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው እንደ ደመሰሳቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ጺባዮ ትሆናለች።


ደግሞም እግዚአብሔርን ለማያመልኩ ሁሉ የመቀጣጫ ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ፈረደባቸው፤


አንዳንዶችን ከእሳት አውጥታችሁ አድኑአቸው፤ ለሌሎች በፍርሃት ራሩላቸው፤ ሆኖም በኃጢአት የረከሰውን ሰውነታቸውን የነካውን ልብስ እንኳ ሳይቀር ጥሉ።


በዚሁ ዐይነት ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችም ሴሰኞች ሆኑ፤ ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪም ዝሙት ፈጸሙ። ስለዚህ እነርሱ በዘለዓለም እሳት ለሚቀጡት ምሳሌ ሆነዋል።


በእነዚህ መቅሠፍቶች ከሞት የተረፉት የሰው ዘር ከእጃቸው ሥራ ተመልሰው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወርቅ፥ ከብር፥ ከናስ፥ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖቶች ማምለክንም አልተዉም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos