አሞጽ 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 “ሰብላችሁን የሚያደርቅ ብርቱ ነፋስ ላክሁባችሁ፤ አትክልታችሁንና የወይን ተክላችሁን የበለስና የወይራ ዛፋችሁን ሁሉ አንበጣ በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 “የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤ በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤ አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 “በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፤ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በአባርና በቸነፈር መታኋችሁ፤ አትክልታችሁ፥ ወይናችሁና በለሳችሁ፥ ወይራችሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እናንተ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፥ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በልቶአል፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። Ver Capítulo |