ከመማረክና ከመገደል እንዴት ታመልጣላችሁ? ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እናንተን ለመቅጣት እጁ እንደ ተሰነዘረ ነው።
ኤርምያስ 46:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦች ሁሉ ስለ ኀፍረትሽ ሰምተዋል፤ የዓለምም ሕዝብ ሁሉ ጩኸትሽን አድምጠዋል፤ አንዱ ወታደር ሌላውን ወታደር ሲያደናቅፈው ሁሉም ተያይዞ መሬት ይወድቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቦች ኀፍረትሽን ይሰማሉ፤ ልቅሶሽም ምድርን ይሞላል። ጦረኛ በጦረኛው ይደናቀፋል፤ ሁለቱም ተያይዘው ይወድቃሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ውርደትሽን ሰምተዋል፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጦረኞች በጦረኞች ላይ ተሰናክለው ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ቃልሽን ሰምተዋል፤ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ጕስቍልናሽን ሰምተዋል፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል። |
ከመማረክና ከመገደል እንዴት ታመልጣላችሁ? ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እናንተን ለመቅጣት እጁ እንደ ተሰነዘረ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በግብጽ ምድር የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ አደርጋለሁ፤ ወንድም በወንድሙ ላይ፥ ጐረቤትም በጐረቤቱ ላይ በጠላትነት እንዲነሣ አደርጋለሁ፤ ከተሞች በከተሞች ላይ፥ ነገሥታት በነገሥታት ላይ በጠላትነት ተነሥተው ይዋጋሉ።
“ይሁዳ በሐዘን ላይ ነች፤ ከተሞችዋም በሞት ጣዕር ላይ ናቸው፤ ሕዝብዋም በሐዘን ምክንያት በመሬት ላይ ተቀምጠው ያለቅሳሉ፤ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ትጮኻለች።
ወደ ባዕዳን ሕዝብ አማልክት ዘወር በማለትሽ ራስሽን አቃለሻል፤ ከዚህ በፊት በአሦር ምክንያት ኀፍረት እንደ ደረሰብሽ አሁን ደግሞ በግብጽ ምክንያት ኀፍረት ይደርስብሻል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ውሃ ከሰሜን በኩል ተነሥቶ በጐርፍ እንደ ተሞላ ወንዝ ይፈስሳል፤ ምድርንና በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ከተሞችንና በውስጣቸው የሚኖሩትን ሕዝብ በሙሉ ይሸፍናል። ሕዝቡ ሁሉ ርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ።
“የሐሴቦንና የዔልዓሌ ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ጩኸታቸውም እስከ ያሀጽ ተሰምቶአል፤ ከጾዓር እስከ ሖሮናይምና ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ተሰምቶአል፤ የኒምሪም ውሃ እንኳ ደርቆአል።
እርሱ የጦር ሹማምንቱን ይጠራል፤ እነርሱም እየተደናቀፉ ወደፊት ይመጣሉ፤ የጠላት ወታደሮች እየሮጡ ወደ ከተማይቱ ቅጽር ይወጣሉ፤ የሚወረወርባቸውንም ፍላጻ በትልቁ ጋሻቸው ይከላከላሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ቀን ከኢየሩሳሌም ቅጽር በዓሣ በር በኩል ኡኡታ ይሰማል፤ ከአዲሱም አደባባይ የዋይታ ድምፅ ያስተጋባል፤ በኰረብቶችም አካባቢ ከፍተኛ ሽብር ይሰማል።