Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 14:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ይሁዳ በሐዘን ላይ ነች፤ ከተሞችዋም በሞት ጣዕር ላይ ናቸው፤ ሕዝብዋም በሐዘን ምክንያት በመሬት ላይ ተቀምጠው ያለቅሳሉ፤ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ትጮኻለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ይሁዳ ታለቅሳለች፤ ከተሞቿም ይማቅቃሉ፤ በምድር ላይ ተቀምጠው ይቈዝማሉ፤ ጩኸትም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ይሰማል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ይሁዳ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ፤ ስለ ምድሪቱም አለቀሱ፤ የኢየሩሳሌም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሏል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ይሁዳ አለ​ቀ​ሰች፤ ደጆ​ች​ዋም ባዶ ሆኑ፤ በም​ድ​ርም ላይ ጨለሙ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎ​አል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ይሁዳ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ በምድርም ላይ ጨለሙ፥ የኢየሩሳሌም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎአል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 14:2
30 Referencias Cruzadas  

ድኾችን በመጨቈን ወደ እግዚአብሔር እንዲጮኹ አድርገዋቸዋል፤ እግዚአብሔርም የድኾችን ጩኸት ሰምቶአል።


ከብቶቻችን የሰቡ ይሁኑ፤ ሳይጨነግፉም በመርባት ይብዙ፤ በመንገዶቻችን የሐዘን ጩኸት ከቶ አይሰማ።


ጭንቀት የተሞላበትን ጩኸታቸውንም ሰምቶ እግዚአብሔር ከአብርሃም፥ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን አስታወሰ።


ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።


ዳግመኛ የወይን ጠጅ ስለማይገኝ ሰዎች በየአደባባዩ ይጮኻሉ፤ ደስታ ለዘለዓለም ጠፍቶአል፤ ሐሴትም በምድር ላይ አይገኝም፤


ምድሪቱ እጅግ ደርቃ ልምላሜዋ ሁሉ ይጠወልጋል፤ የምድርም ታላላቅ ሰዎች ይደክማሉ።


የወይን ተክሎች ደርቀዋል፤ የወይን ጠጅም ተወዶአል፤ በዚህ ምክንያት ከዚህ በፊት ይደሰት የነበረ ሁሉ አሁን ሐዘንተኛ ሆኖአል፤


የኢየሩሳሌም በሮች እርቃንዋን ሆና በልቅሶና በሐዘን እንደ ተቀመጠች ሴት ይሆናሉ።


ምድሪቱም ደርቃለች፤ ባድማ ሆናለች፤ የሊባኖስ ደኖች ደርቀዋል፤ ለሙ የሳሮን ሸለቆ ወደ በረሓነት ተለውጦአል፤ በባሳንና በቀርሜሎስ ተራራዎች የሚገኙ ዛፎች ቅጠላቸው ረግፎአል።


ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።


ስለዚህም እነሆ እኔ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ ከጥፋቱም ማምለጥ አይችሉም፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት ቢጮኹም እንኳ አልሰማቸውም።


ምድረ በዳም ስላደረጉአት በፊቴ ባድማ ሆናለች፤ አገሪቱ በሙሉ ወደ በረሓነት ተለውጣለች፤ ስለ እርስዋም የሚገደው አንድ እንኳ የለም።


“እኛ የምናደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አያይም” ከሚሉት ሕዝባችን ክፋት የተነሣ፥ ምድራችንን ድርቅ የሚያጠቃውና በየመስኩ ያለውስ ሣር እንደ ደረቀ የሚቀረው እስከ መቼ ነው? በዚህም ምክንያት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ተጠራርገው ጠፍተዋል።


ወራሪዎችን በድንገት ላክባቸው፤ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ፤ እነርሱ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቆፍረዋል፤ የምያዝበትንም ወጥመድ አዘጋጅተዋል።


ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማይም በጨለማ ይጋረዳል፤ ይህን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ሐሳቡም አይለወጥም፤ ቊርጥ ውሳኔ አድርጎአል፤ ወደ ኋላም አይመለስም።


ሕዝቦች ሁሉ ስለ ኀፍረትሽ ሰምተዋል፤ የዓለምም ሕዝብ ሁሉ ጩኸትሽን አድምጠዋል፤ አንዱ ወታደር ሌላውን ወታደር ሲያደናቅፈው ሁሉም ተያይዞ መሬት ይወድቃል።


ሕዝቤ በመሰበሩ የእኔም ልብ ተሰብሮአል፤ ፍርሀትም ይዞኝ አለቅሳለሁ።


እግዚአብሔር የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጽር ለማፍረስ ወስኖ ገመዱን ዘረጋ፤ ከማጥፋት አልተመለሰም፤ የመጠበቂያ ግንቡና ቅጽሩ ተፈረካከሱ፤ በአንድነትም ፈረሱ።


የቅጽር በሮች ከመሬት በታች ተቀበሩ፤ መወርወሪያዎቻቸውም ተሰባብረው ወደቁ፤ ንጉሡና መሳፍንቱ አሁን በአሕዛብ መካከል በስደት ላይ ናቸው፤ የኦሪት ሕግ ትምህርት ከእንግዲህ ወዲህ አይሰጥም፤ ነቢያትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አይገለጥላቸውም።


ከራብ ጽናት የተነሣ ቆዳችን እንደ ምድጃ ጠቈረ።


በዚህም ምክንያት በምድሪቱ ላይ ድርቅ ይመጣል፤ በእርስዋ የሚኖሩ ሁሉ ይደክማሉ፤ እንስሶች፥ ወፎችና የባሕር ዓሣዎች ሁሉ ያልቃሉ።”


እርሻዎች ባዶአቸውን ቀርተዋል፤ እህል ጠፍቶአል፤ የወይን ተክሎች ደርቀዋል፤ ዘይትም ጠፍቶአል፤ ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች።


ስንዴውና ገብሱ፥ ሌላውም መከር ሁሉ ስለ ጠፋ፥ እናንተ ገበሬዎች እዘኑ፤ እናንተም የወይን ተክል ባለቤቶች አልቅሱ።


የተለየ የጾም ቀን ዐውጁ! መንፈሳዊ ስብስባ ጥሩ! ሽማግሌዎችንና ሌሎችንም የአገሪቱን ኗሪዎች ሁሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ በዚያም ወደ እግዚአብሔር ጩኹ።


እነርሱን በሚያዩበት ጊዜ ሕዝቦች ይርበደበዳሉ፤ የሰውም ሁሉ ፊት በፍርሃት ይገረጣል።


እነሆ በዚህ ምክንያት በተራሮች ላይ በእህል፥ በወይን፥ በዘይት፥ ምድር በምታበቅለው ሁሉ ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶች፥ በሥራቸውም ውጤት ሁሉ ላይ ድርቅን አመጣለሁ።”


እኔ ስናገር ‘አናዳምጥም’ ስላሉ፥ እነርሱም ወደ እኔ በጸለዩ ጊዜ መልስ አልሰጠኋቸውም ይላል የሠራዊት አምላክ።


ከሞት የተረፉትም የእባጩ በሽታ በርትቶባቸው ስለ ነበር ሕዝቡ ርዳታ ለማግኘት ወደ አማልክታቸው በማልቀስ ጮኹ።


“ነገ በዚህ ሰዓት ከብንያም አገር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፤ ጩኸታቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ ወደ ሕዝቤ ተመልክቼአለሁና ከፍልስጥኤማውያን ጭቈና ሕዝቤን ስለሚያድን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አድርገህ ቀባው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos