ኤርምያስ 4:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማይም በጨለማ ይጋረዳል፤ ይህን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ሐሳቡም አይለወጥም፤ ቊርጥ ውሳኔ አድርጎአል፤ ወደ ኋላም አይመለስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማያትም በላይ ይጨልማሉ፤ ተናግሬአለሁ፤ ሐሳቤን አልለውጥም፤ ወስኛለሁ፤ ወደ ኋላም አልልም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠቁራል፤ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፤ በላይም ሰማይ ይጠቍራል፤ ተናግሬአለሁና፤ አልጸጸትም ወደፊት እሮጣለሁ፤ ከእርስዋም አልመለስም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠቍራል፥ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፥ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም። |
ፀሐይ፥ ጨረቃና ከዋክብት ሁሉ ይጠፋሉ፤ ሰማይም እንደ ብራና ተጠቅሎ ይወገዳል፤ ከዋክብትም እንደ ወይንና እንደ በለስ ዛፍ ቅጠል ይረግፋሉ።
በዚያን ቀን እንደ ባሕር ማዕበል እየተመሙ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ይመጡባቸዋል፤ እነሆ ወደ ምድር ቢመለከቱ በጨለማና በመከራ እንደ ተከበቡ ያያሉ፤ ከደመናውም የተነሣ ብርሃኑ ይጨልማል።
“እኛ የምናደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አያይም” ከሚሉት ሕዝባችን ክፋት የተነሣ፥ ምድራችንን ድርቅ የሚያጠቃውና በየመስኩ ያለውስ ሣር እንደ ደረቀ የሚቀረው እስከ መቼ ነው? በዚህም ምክንያት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ተጠራርገው ጠፍተዋል።
“ይሁዳ በሐዘን ላይ ነች፤ ከተሞችዋም በሞት ጣዕር ላይ ናቸው፤ ሕዝብዋም በሐዘን ምክንያት በመሬት ላይ ተቀምጠው ያለቅሳሉ፤ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ትጮኻለች።
ምድሪቱ እግዚአብሔርን በተዉ አመንዝሮች ተሞልታለች፤ ነቢያቱ ኀይላቸውን ያለ አግባቡ ይጠቀማሉ፤ የክፋትንም መንገድ ይከተላሉ፤ ከእግዚአብሔር ርግማን የተነሣ፥ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ መስኮችም ደርቀዋል።
በባቢሎን ቅጥር ላይ አደጋ ጣሉ የሚል ምልክት አሳዩ! ጥበቃውን አጠናክሩ! ሰላዮችን መድቡ! ደፈጣ ተዋጊዎችንም አዘጋጁ፤ ይህንንም የምታደርጉት እግዚአብሔር በባቢሎን ሕዝብ ላይ ያቀደውንና የተናገረውን ተግባራዊ ስለሚያደርግ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤርምያስ ሆይ! ስለ ነዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ስለ እነርሱ በመጸለይም አትጩኽ፤ ስለማልማለድህ ስለ እነርሱ ልትማልደኝ አያስፈልግም፤
እግዚአብሔር ያሰበውን ፈጸመ፤ ቀድሞ የተናገረውን ቃል ተግባራዊ አደረገ፤ ከረጅም ጊዜ በፊት በወሰነው መሠረት ያለ ርኅራኄ አፈራረሰ፤ ጠላት በእናንተ ላይ ደስ እንዲሰኝ አደረገ፤ የጠላቶቻችሁንም ኀይል አበረታ።
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ‘አንድ ነገር የማደርግበት ጊዜ ቀርቦአል፤ አልገታም፤ አልምርም፤ ሐሳቤን አለውጥም፤ እንደ አካሄድሽና እንደ ሥራሽ እፈርድብሻለሁ’ ” ብዬ ተናግሬአለሁ።
ከሲኦል ኀይል እታደጋቸዋለሁን? ከሞትስ አድናቸዋለሁን? ሞት ሆይ! መቅሠፍቶችህ የት አሉ? ሲኦል ሆይ! አጥፊነትህ የት አለ? እኔኮ አልራራላቸውም፤
ኢየሱስ ግን ካህን የሆነው በእግዚአብሔር መሐላ ነው፤ ይህም፦ “እግዚአብሔር ‘አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ’ ብሎ ምሎአል፤ አይለውጥም” ተብሎ በተነገረለት መሠረት ነው።
ከዚህ በኋላ በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለከትኩ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይ እንደ ጥቊር የሐዘን ልብስ ጠቈረች፤ ጨረቃም በሙሉ እንደ ደም ቀላች፤