ኢሳይያስ 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ሁሉ የግፍ ሥራችሁ እግዚአብሔር እናንተን በሚቀጣበት ጊዜ ምን ታደርጉ ይሆን? በእናንተ ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ከሩቅ አገር በሚያመጣበት ጊዜስ ምን ይበጃችሁ ይሆን? ርዳታስ ለማግኘት የምትሄዱት ወደማን ነው? ሀብታችሁንስ የት ትሸሽጉታላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምትጐበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተጐበኛችሁበት ቀን፥ ምን ታደርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመጣባችኋልና፥ ለረድኤትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተጐበኛችሁበት ቀን፥ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን? ለረድኤትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ክብራችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ? |
ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ።
በእግዚአብሔር ፊት ለፍርድ በቆምኩ ጊዜ ምን ይበጀኝ ይሆን? በፍርድ በሚመረምረኝስ ጊዜ ለሚያቀርብልኝ ጥያቄ ምን መልስ መስጠት እችል ይሆን?
በዚያን ጊዜ በባሕር ዳርቻ የሚኖሩ ሰዎች፦ ‘እኛን ከአሦር ንጉሠ ነገሥት ያድኑናል ብለን ተስፋ ያደረግንባቸውና ወደ እነርሱ የተጠጋንባቸው አገሮች ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እኛማ እንዴት እናመልጣለን?’ ” ይላሉ።
በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም።
የሚከተለው ምሳሌ እንደ ተነገረበት ሰው ትሆናላችሁ፤ ይህም ሰው በጣም አጭር በሆነ ድንክ አልጋ ላይ ተኝቶ እግሩን መዘርጋት ተሣነው፤ ልብሱም ጠባብ ከመሆኑ የተነሣ ሰውነቱን በሙሉ መሸፈን አልቻለም።
የሠራዊት ጌታ አምላክ ነጐድጓድን፥ የመሬት መናወጥን፥ ታላቅ ድምፅን፥ ዐውሎ ነፋስን፥ ሞገድንና የሚባላ የእሳት ነበልባልን በጠላቶችሽ ላይ በመላክ አንቺን ይታደግሻል።
በዚህ ፈንታ በፈጣን ፈረሶች ላይ ተቀምጣችሁ ከጠላቶቻችሁ እጅ ለማምለጥ ታቅዳላችሁ፤ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ‘ፈረሶቻችን እጅግ ፈጣኖች ናቸው’ ትሉ ይሆናል፤ ነገር ግን አሳዳጆቻችሁ ከእናንተ የፈጠኑ ይሆናሉ።
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ።
በዚያም ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ “እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?” ብሎ ጠየቀው። ሕዝቅያስም “እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው” ሲል መለሰለት።
እርሱን የሚያፈራርሱ ሰዎችን እልካለሁ፤ እነርሱም መጥረቢያቸውን ይዘው ይመጣሉ፤ ከተዋበ የሊባኖስ ዛፍ የተሠሩትንም ዐምዶች ቈራርጠው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል።
ለጥፋት የተዳረግሽ ኢየሩሳሌም ሆይ! ወዮልሽ! ቀይ ልብስ የለበስሽበት ምክንያት ምንድን ነው? ጌጣጌጥ ማድረግሽና ዐይንሽንስ መኳልሽ ለምንድነው? ውሽሞችሽ ጠልተውሽ ሊገድሉሽ ስለሚፈልጉ ውበትሽን የምትንከባከቢው በከንቱ ነው።
ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”
“እስራኤል መታመሙን፥ ይሁዳም መቊሰሉን ባየ ጊዜ፥ እስራኤል ወደ አሦር ፊቱን መለሰ፤ ርዳታም ለማግኘት ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ ነገር ግን እርሱ ሊያድናቸው ወይም ቊስላቸውን ሊፈውስ አልቻለም።
የቅጣት ቀን ደርሶአል፤ እስራኤላውያንም የበቀል ቀን መቃረቡን ይወቁ፤ በእናንተ በደልና ጥላቻ ምክንያት ነቢይን እንደ ሞኝ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረበትን ሰው እንደ ዕብድ ትቈጥሩታላችሁ።
ያ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሸሽቶ ሲሄድ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወይም አምልጦ ወደ ቤቱ ሲገባ እጁን በግድግዳ ላይ ቢያሳርፍ እባብ እንደሚነድፈው ሁኔታ ይሆንባችኋል።
ከእነርሱ መካከል እጅግ የተሻለ ነው የተባለው ሰው እንደ አሜከላ ነው፤ እጅግ ትክክለኛ ነው የተባለው እንደ ኲርንችት ነው፤ በነቢያቱ አማካይነት ባስጠነቀቃቸው መሠረት እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚቀጣበት ጊዜ ይመጣል፤ እነሆ አሁንም ቢሆን በሽብር ላይ ይገኛሉ።
እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።
አንቺንና በውስጥሽ ያሉትንም ልጆችሽን በመሬት ላይ ጥለው ያወድማሉ፤ ሳይፈርስ የሚቀር አንድ ድንጋይ እንኳ በቦታው አይተዉልሽም፤ ይህም የሚሆነው፥ እግዚአብሔር አንቺን ሊያድን የመጣበትን ጊዜ ባለማወቅሽ ነው።”
ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ቀን አሕዛብ መልካም ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በእነርሱ መካከል ስትኖሩ መልካም ጠባይ ይኑራችሁ።