Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 13:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጥፋትን የሚያመጣበት ቀን ስለ ተቃረበ “ዋይ! ዋይ!” እያላችሁ አልቅሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና አልቅሱ፤ ሁሉን ቻይ ከሆነ አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የጌታ ቀን ቀርቦአልና አልቅሱ፤ ሁሉን ቻይ ከሆነ አምላክ ቀኑ እንደ ጥፋት ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና አል​ቅሱ፤ ጥፋ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይመ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ አልቅሱ፥ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 13:6
39 Referencias Cruzadas  

ወዮ! የጌታ ቀን ቀርቦአል! ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጥፋትን የሚያመጣበት ቀን ደርሶአል። ስለዚያ ቀን ወዮ!


የእግዚአብሔር ፍርድ ቀን ስለ ቀረበ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመሥዋዕት እንደሚታረድ እንስሳ አሳልፎ ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው፤ ይሁዳን የሚበዘብዙ ጠላቶችንም ለይቶ አዘጋጅቶአል።


እናንተ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት የምትጠባበቁ ወዮላችሁ! ያ ቀን የጨለማ እንጂ የብርሃን ቀን ስላይደለ ለምን ያንን ቀን ትጠባበቃላችሁ?


እነሆ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቊጣና መዓት የሚፈጸምበት ያ ቀን እጅግ አስፈሪ ነው፤ በዚያን ጊዜ በእርስዋ የሚኖረው ኃጢአተኛ ሕዝብ ስለሚደመሰስ ምድሪቱ ባድማ ትሆናለች።


ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ አንቺ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን ሆይ! ፍርድሽ በአንድ ሰዓት ውስጥ ስለ መጣ፥ ወዮልሽ! ወዮልሽ!” ይላሉ።


እግዚአብሔር እንደ ነጐድጓድ ያለ ድምፁን በሠራዊቱ ላይ ያሰማል፤ ሠራዊቱ ምንኛ ብዙ ነው! ትእዛዙን የሚቀበሉ ከቊጥር በላይ ናቸው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ ነው፤ በጣም አስፈሪ ስለ ሆነ በዚያ ቀን ማን ችሎ ይቆማል?


ባቢሎን በድንገት ወድቃ ተሰብራለችና አልቅሱላት፤ ምናልባት ይፈወስ እንደ ሆነ ለቊስልዋ የሚቀባ መድኃኒት ፈልጉ።


እግዚአብሔር ለጽዮን ለመከላከልና የበቀል እርምጃ ለመውሰድ የሚመጣበትን ዓመትና ቀን ወስኖአል።


የሠራዊት አምላክ ትዕቢተኞችና ኩራተኞች የሚዋረዱበትን ቀን ወስኖአል።


አሁን ደግሞ እናንተ ሀብታሞች! ኑ አድምጡ፤ አሠቃቂ መከራ ስለሚመጣባችሁ እየጮኻችሁ አልቅሱ።


“ታላቁና አስፈሪው የእኔ የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት እነሆ፥ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።


ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ አመጣጡም እየፈጠነ ነው፤ ያ ቀን እጅግ አስፈሪ ነው፤ በዚያን ቀን የሚሰማው ድምፅ አስከፊ ነው፤ ተዋጊው በከፍተኛ ድምፅ ይጮኻል።


ታላቁና አስፈሪው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ደም ትመስላለች፤


ለአምላካችሁ የምታቀርቡት የእህልም ሆነ የወይን ጠጅ መባ ስለሌለ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች የሆናችሁ ካህናት! ኑና ማቅ ለብሳችሁ ሌሊቱን ሁሉ አልቅሱ! እናንተም በመሠዊያው ላይ የምታገለግሉ ዋይ! ዋይ! በሉ።


ከእንግዲህ ወዲህ አዲስ የወይን ጠጅ በአፋችሁ ስለማትቀምሱ፥ እናንተ ሰካራሞች ከእንቅልፋችሁ ነቅታችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የወይን ጠጅ መጠጣት የምታዘወትሩ ምርር ብላችሁ አልቅሱ።


በመግቢያው በር ሆናችሁ ወዮ በሉ! በከተማው ውስጥ ሆናችሁ ኡኡ! በሉ፤ ከወታደሮቹ አንዱ እንኳ ወደ ኋላ የማይል ኀይለኛ ጠላት ከሰሜን ስለ መጣ ፍልስጥኤማውያን ሁሉ በፍርሃት ይርበድበዱ!


የእግዚአብሔርን መቅሠፍት እፈራለሁ፤ ከግርማውም አስፈሪነት የተነሣ በፊቱ መቆም አልችልም።


ስንዴውና ገብሱ፥ ሌላውም መከር ሁሉ ስለ ጠፋ፥ እናንተ ገበሬዎች እዘኑ፤ እናንተም የወይን ተክል ባለቤቶች አልቅሱ።


የሰው ልጅ ሆይ! በሐዘን ጩኽ፤ ይህ ሰይፍ የተዘጋጀው ሕዝቤንና የእስራኤልን መሪዎች ለማጥፋት ነው። እነርሱም ከቀሩት ሕዝቤ ጋር ይገደላሉ፤ ስለዚህ በሐዘን ደረትህን ምታ።


የዐይ ከተማ ስለ ፈረሰች አልቅሱ! በራባ ከተማ አካባቢ መንደሮች የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ጮክ ብላችሁ አልቅሱ! ሚልኮም የተባለው ጣዖት ከካህናቱና ከረዳቶቹ ጋር ተማርኮ የሄደ ስለ ሆነ ማቅ ለብሳችሁ በቅጥሮችዋ መካከል ወዲያና ወዲህ እያላችሁ አልቅሱ!


አገልጋዮቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፤ እናንተ ግን ከልብ ሐዘን የተነሣ ታላቅሳላችሁ፤ ከመንፈስም ጭንቀት የተነሣ ዋይ፥ ዋይ ትላላችሁ።


“ሕዝቤ ያለ ዋጋ ሲወሰድ እያየሁ አሁን እኔ የማደርገው ምን አለ? ገዢዎቻቸውም ይሳለቁባቸዋል፤ ያለማቋረጥም ስሜን ይሰድባሉ።


ስለ ጢሮስ ከተማ የተነገረ የትንቢት ቃል ይህ ነው፤ ጢሮስና ቤትዋ ወይም ወደብዋ የፈራረሱ ስለ ሆነ እናንተ የተርሴስ መርከቦች እሪ በሉ፤ ከቆጵሮስ ስትመለሱ የሚጠብቃችሁ ወሬ ይኸው ነው።


“እናንተ መሪዎች አልቅሱ፤ እናንተ የሕዝብ ጠባቂዎች ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ‘ዋይ፥ ዋይ!’ በሉ፤ በዐመድ ላይ እየተንከባለላችሁ እዘኑ፤ ሁላችሁም የምትታረዱበት ጊዜ ደርሶአል፤ ውድ የሆነ የሸክላ ዕቃ ሲወድቅ ተሰብሮ እንደሚበታተን፥ እናንተም ትበታተናላችሁ።


በዚህ ሁሉ የግፍ ሥራችሁ እግዚአብሔር እናንተን በሚቀጣበት ጊዜ ምን ታደርጉ ይሆን? በእናንተ ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ከሩቅ አገር በሚያመጣበት ጊዜስ ምን ይበጃችሁ ይሆን? ርዳታስ ለማግኘት የምትሄዱት ወደማን ነው? ሀብታችሁንስ የት ትሸሽጉታላችሁ?


ከጥቂት ጊዜ በኋላ በእናንተ ላይ ያለኝ ቊጣ ይቆማል፤ ከዚያን በኋላ እነርሱን እደመስሳለሁ።


ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”


እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ላይ ተቈጥቶአል፤ ኀይለኛ ቊጣውም በሠራዊቶቻቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ፈጽሞ ያጠፋዋል፤ በሰይፍም እንዲገደሉ አሳልፎ ይሰጣቸዋል።


በመተትሽ ልታስወግጂ የማትችይው ክፉ ነገር ይመጣብሻል፤ ልትከላከዪ የማትችይው ችግር ይደርስብሻል፤ ምንም ያላሰብሽው ጥፋት በድንገት ያጋጥምሻል።


የእግዚአብሔርን የምሕረት ዓመትና የአምላካችንን የበቀል ቀን እንዳውጅ፥ የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና፥


በእግዚአብሔር ቀን ጦርነቱን ለመቋቋም ይቻል ዘንድ ወደ ፍርስራሹ አልወጣችሁም፤ ወይም የእስራኤልን ቅጥር አልጠገናችሁም።


ንጉሥ ብልጣሶር እጅግ ስለ ጨነቀው ፊቱ ይብሱን እየገረጣ ሄደ፤ መኳንንቱም ግራ ገብቶአቸው የሚያደርጉትን አጡ።


ትርጒሙም የሚከተለው ነው፤ ማኔ ‘እግዚአብሔር የመንግሥትህን ዘመን ቈጥሮ እንዲፈጸም አደረገው’ ማለት ነው።


የእግዚአብሔር ፍርድ ቀን ደርሶአል፤ በዚያን ጊዜ ዐይናችሁ እያየ በዝባዦች ከእናንተ የወሰዱትን ይካፈሉታል።


የምበቀልበትን ጊዜ ወስኜአለሁ፤ ሕዝቤን የምታደግበትም ጊዜ ደርሶአል።


በጽዮን መለከት ንፉ! በተቀደሰው ተራራውም ላይ የእሪታ ድምፅ አሰሙ! የጌታ ቀን መምጫ ስለ ተቃረበ በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios