Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 29:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የሠራዊት ጌታ አምላክ ነጐድጓድን፥ የመሬት መናወጥን፥ ታላቅ ድምፅን፥ ዐውሎ ነፋስን፥ ሞገድንና የሚባላ የእሳት ነበልባልን በጠላቶችሽ ላይ በመላክ አንቺን ይታደግሻል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በነጐድጓድ፣ በምድር መናወጥና በታላቅ ድምፅ፣ በዐውሎ ነፋስና በኀይለኛ ሞገድ፣ ፈጽሞ በሚባላም የእሳት ነበልባል ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ድን​ገ​ትም ፈጥኖ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ጐ​ድ​ጓድ፥ በም​ድ​ርም መና​ወጥ፥ በታ​ላቅ ድምፅ፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በወ​ጨ​ፎም፥ በም​ት​በ​ላም በእ​ሳት ነበ​ል​ባል ይጐ​በ​ኛ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 29:6
23 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ከሰማይ አንጐዳጐደ፤ ልዑል እግዚአብሔር ድምፁን አሰማ።


ከዚህ ከደረሰብኝ ዐውሎ ነፋስና ሞገድ መጠለያ ስፍራ ለማግኘት ፈጥኜ በሄድኩ ነበር።


በዚህ ሁሉ የግፍ ሥራችሁ እግዚአብሔር እናንተን በሚቀጣበት ጊዜ ምን ታደርጉ ይሆን? በእናንተ ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ከሩቅ አገር በሚያመጣበት ጊዜስ ምን ይበጃችሁ ይሆን? ርዳታስ ለማግኘት የምትሄዱት ወደማን ነው? ሀብታችሁንስ የት ትሸሽጉታላችሁ?


እነዚያ ሁሉ ሞተዋል፤ ዳግመኛም በሕይወት አይኖሩም፤ አንተም ቀጥተሃቸው ስለ ተደመሰሱ፥ ዳግመኛ አይነሡም፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል።


በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም።


እነሆ፥ ጌታ እንደ በረዶ ወጨፎ፥ እንደሚያጠፋ ዐውሎ ነፋስና እንደሚያጥለቀልቅ ኀይለኛ የውሃ ጐርፍ የሆነ አንድ ጠንካራና ኀያል ሰው አለው። ይህም ሰው በሥልጣኑ ወደ ምድር አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል።


እግዚአብሔር ክቡር ድምፁን እንዲሰሙ ያደርጋል። በኀይለኛ ቊጣው፥ በሚያቃጥል የእሳት ነበልባል፥ በመብረቅ፥ በወጀብና በጠጣር በረዶ የሚወርደው ኀይለኛ ቅጣቱ እንዲታይ ያደርጋል።


ሽብር በተነሣ ጊዜ ምሽጋቸው ይፈርሳል፤ የጦር መኰንኖቻቸውም አርማቸውን ትተው በመርበድበድ ይሸሻሉ”። እሳቱ በጽዮን፥ እቶኑ በኢየሩሳሌም የሆነው እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።


በቸነፈርና በግድያ እንዲቀጣ እፈርድበታለሁ፤ በእርሱ ላይ፥ በወታደሮቹ ላይና ከእርሱ ጋር በነበሩት ሰዎች ላይ የዝናብ ዶፍ፥ የበረዶ ናዳ፥ እሳትና ዲን አዘንብባቸዋለሁ።


ስለዚህ በራባ ከተማ ቅጽር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ ምሽጎችዋንም ያቃጥላል፤ ከዚህ በኋላ በጦርነቱ ቀን ጩኸትና ሁካታ ይበዛል፤ ጦርነቱም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይፈጥናል፤


እግዚአብሔር ታጋሽና ኀያል ነው፤ ነገር ግን በደለኛውን ሳይቀጣው አያልፍም፤ መንገዱ በዐውሎ ነፋስና በሞገድ ውስጥ ነው፤ ሰው ሲራመድ ትቢያን እንደሚያስነሣ፥ የእግዚአብሔርም መገለጥ ደመናን ያስከትላል።


እናንተም ተራራውን በሁለት ከፍሎ እስከ አጻል በደረሰው በዚህ ሸለቆ ውስጥ አልፋችሁ ታመልጣላችሁ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ምድር በተናወጠች ጊዜ የቀድሞ አባቶቻችሁ በሸሹት ዐይነት ትሸሻላችሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬም ቅዱሳኑን አስከትሎ ይመጣል።


ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ በጦርነት ይነሣል፤ በልዩ ልዩ ስፍራ ራብና የምድር መናወጥ ይሆናል።


ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ጦርነት ያነሣል፤ በየስፍራው የምድር መናወጥና ራብ ይሆናል፤ ይህ ሁሉ እንደ ምጥ ጣር ያለ የጭንቅ መጀመሪያ ነው።


በየቦታውም ብርቱ የምድር መናወጥ፥ ራብና ወረርሽኝ ይሆናል። የሚያስፈሩ ነገሮችና ታላላቅ ምልክቶች በሰማይ ላይ ይታያሉ።


በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ፈራረሰ፤ በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ የሰማይንም አምላክ አከበሩ።


በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።


መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ይህን የመሰለ ታላቅ የምድር መናወጥ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ ሆኖ አያውቅም።


እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደመሰሳሉ፤ ከሰማይም ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ይፈርዳል፤ ለንጉሥም ኀይልን ይሰጠዋል፤ ለመረጠውም ክብሩን ከፍ ከፍ ያደርግለታል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos