ሆሴዕ 9:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱን ስላልታዘዙ አምላኬ ይጥላቸዋል፤ እነርሱም በአሕዛብ መካከል በመንከራተት ይኖራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለመታዘዛቸው ምክንያት፣ አምላኬ ይጥላቸዋል፤ በአሕዛብም መካከል ተንከራታች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱን አልሰሙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል፤ በአሕዛብም መካከል ተቅበዝባዦች ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አልሰሙትምና እግዚአብሔር ይጥላቸዋል፤ በአሕዛብም መካከል ተቅበዝባዦች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አልሰሙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል፥ በአሕዛብም መካከል ተቅበዝባዦች ይሆናሉ። |
እስራኤላውያን ግን በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ በነቢያቱም በማፌዝ፥ የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ ወረደ፤ ከታላቅ ቊጣውም ለማምለጥ አልቻሉም።
“ትእዛዞቼን በጥንቃቄ ሰምታችሁ ቢሆንማ ኖሮ፥ በረከታችሁ እንደማይደርቅ የወንዝ ውሃ፥ ጽድቃችሁም እንደ ባሕር ሞገድ በብዛት በመጣላችሁ ነበር!
ለዚህም ኢሳይያስ ሲመልስ እንዲህ አለ “እናንተ የንጉሥ ዳዊት ቤተሰብ ሆይ! ስሙ፤ ሰውን ማሰልቸታችሁ አንሶ እግዚአብሔርንስ ማሳዘን ትፈልጋላችሁን?
ሕዝቤ እኔን በሚገባ ካለማወቁ የተነሣ ጠፍቶአል፤ እናንተ እኔን ለማወቅ ስላልፈለጋችሁ እኔም ካህናት ሆናችሁ እንድታገለግሉኝ አልፈልጋችሁም፤ ሕጌንም ስላቃለላችሁና ስለ ረሳችሁ ልጆቻችሁ በእኔ ዘንድ የተረሱ ይሆናሉ።
“ከእኔ ርቀው ስለ ሄዱ ወዮላቸው! በእኔም ላይ ስለ ዐመፁ ጥፋት ይምጣባቸው፤ እኔ ልታደጋቸው ፈልጌ ነበር፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።
እግዚአብሔርም “ይህ የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልኩት። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ እነርሱን ከመቅጣት አልመለስም።
“የእስራኤል ሕዝብ በሕዝቦች መካከል እንዲበተኑ አዛለሁ፤ የሚበተኑትም እህል በወንፊት እንደሚነፋ ዐይነት ነው፤ ነገር ግን ወንፊቱ ሲነቃነቅ ገለባው እንጂ አንድም ቅንጣት አይበተንም።
እንደ ቀድሞ አባቶቻችሁ አትሁኑ፤ እነርሱን የቀድሞ ነቢያት ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ’ ብለው አስጠንቅቀዋቸው ነበር፤ አባቶቻችሁ ግን ቃሌን አላደመጡም፤ ትእዛዜንም አልጠበቁም።
ኢየሱስ “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጂና ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፥ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብሎአል’ ብለሽ ንገሪያቸው” አላት።
ስለዚህ የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች እንዲህ ተባባሉ፦ “እኛ እንዳናገኘው ይህ ሰው ወዴት ሊሄድ ነው? ምናልባት በግሪኮች መካከል ወደ ተበተኑት አይሁድ ዘንድ ሄዶ አሕዛብን ያስተምር ይሆን?
“ልጆችና የልጅ ልጆች ኖሮአችሁ በምድሪቱ በደስታ በምትኖሩበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን በምንም ዐይነት ቅርጽ ጣዖት በመሥራት ረክሳችሁ እግዚአብሔርን አታስቈጡት፤
በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሆነው ከያዕቆብ የተላከ መልእክት፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን።