“ለጌታዬ ያለውን ታማኝነትና ዘለዓለማዊ ፍቅር የጠበቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በቀጥታ መርቶ ወደ ጌታዬ ዘመዶች ቤት ያመጣኝ እርሱ ነው” አለ።
ዘፍጥረት 32:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ላይ አደጋ በመጣል ሴቶችና ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ያጠፋናል ብዬ ስለ ፈራሁ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፥ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናትን ከልጆችዋ ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። |
“ለጌታዬ ያለውን ታማኝነትና ዘለዓለማዊ ፍቅር የጠበቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በቀጥታ መርቶ ወደ ጌታዬ ዘመዶች ቤት ያመጣኝ እርሱ ነው” አለ።
አባቱ ስለ መረቀው ዔሳው ያዕቆብን አጥብቆ ጠላው፤ በልቡም “አባቴ በቅርብ ቀን ይሞታል፤ ከዚያ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ” ብሎ አሰበ።
ነገር ግን ርብቃ የዔሳውን ዕቅድ ስለ ሰማች፥ ያዕቆብን ጠርታ እንዲህ አለችው፤ “አድምጠኝ፤ ወንድምህ ዔሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ አስቦአል፤
በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እጅግ በመፍራት ተጨነቀ፤ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች በሁለት ክፍል መደባቸው፤ እንዲሁም በጎቹን፥ ፍየሎቹን፥ ከብቶቹንና ግመሎቹን በሁለት በሁለት መደባቸው።
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እስከዚህ ድረስ ያደረስከኝ፤ እኔ ማን ነኝ? ቤተሰቤስ ምንድን ነው?
በሕዝባችሁ ላይ ከባድ ጦርነት ይመጣል፤ ምሽጎቻችሁ ሁሉ ይፈራርሳሉ፤ ይህም ንጉሥ ሸልማን የቤትአርቤልን ከተማ በጦርነት እንዳፈራረሰና እናቶችን ከልጆቻቸው ጋር በምድር ላይ ፈጥፍጦ እንደ ጨረሰበት ጊዜ ይሆናል።
“አንዲት ወፍ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ጫጩቶችዋንም ሆነ እንቊላሎችዋን ዐቅፋ የተቀመጠችበትን ጎጆ ብታገኝ፥ እናቲቱን ወፍ ከነጫጩቶችዋ አትውሰድ፤
ከዚያም በኋላ እነርሱ ‘አንተን ትተን በዓልንና ዐስታሮትን በማምለካችን በድለናል፤ አሁንም ከጠላቶቻችን አድነን፤ እናመልክህማለን!’ ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
እግዚአብሔር ይፍረድ፤ ከሁለታችንም ስሕተተኛው ማን እንደ ሆነ እርሱ ይወስን፤ እግዚአብሔር ይህን ጉዳይ ተመልክቶ ይከላከልልኝ፤ ከአንተም እጅ ያድነኝ።”