ስለዚህ በዚያን ቀን በእግዚአብሔር ፊት እየበሉና እየጠጡ እጅግ ደስ ተሰኙ። ለሁለተኛ ጊዜም ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን አረጋገጡ፤ በእግዚአብሔር ስም ቀብተው ንጉሣቸው አደረጉት፤ ሳዶቅንም ቀብተው ካህናቸው አደረጉት፤
ዘዳግም 12:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም በባረካችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ሁሉ ተሰብስባችሁ ትበላላችሁ፤ በድካማችሁ ያገኛችሁትን መልካም ነገር ሁሉ ትደሰቱበታላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትበላላችሁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን በባረከበት፣ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተ ሰዎችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ብሉ፤ እጃችሁንም በምትዘረጉበት፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በባረካችሁ ነገር ሁሉ፥ እናንተና ቤተሰባችሁ ደስ ይበላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ብሉ፥ እጃችሁንም በምትዘረጉበት፥ አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ ነገር ሁሉ፥ እናንተና ቤተሰባችሁ ደስ ይበላችሁ። |
ስለዚህ በዚያን ቀን በእግዚአብሔር ፊት እየበሉና እየጠጡ እጅግ ደስ ተሰኙ። ለሁለተኛ ጊዜም ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን አረጋገጡ፤ በእግዚአብሔር ስም ቀብተው ንጉሣቸው አደረጉት፤ ሳዶቅንም ቀብተው ካህናቸው አደረጉት፤
የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ሰዎቹ ስላለቀሱ፥ አገረ ገዢው ነህምያ፥ ካህኑና የሕግ ምሁሩ ዕዝራ፥ ሕዝቡን ያስተምሩ የነበሩት ሌዋውያን “ይህ ቀን ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን ስለ ሆነ፥ አትዘኑ፤ አታልቅሱም” አሉአቸው።
እንግዲህ እኔ የተመለከትኩት የተሻለ ነገር ቢኖር ሰው በዚህ ዓለም ሳለ እግዚአብሔር በሰጠው አጭር ዕድሜ የደከመበትን ሁሉ በመብላትና በመጠጣት መደሰቱ ነው፤ የሰው ዕድል ፈንታም ይኸው ብቻ ነው።
በንግድ የምታገኘውም ገንዘብ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ ለራስዋ ተቀማጭ ሳታደርግ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሚያስፈልጋቸው ምግብና በጥሩ ልብስ ያውሉታል።
ነገር ግን በጐተራ የሰበሰቡትን እህል እነርሱ ራሳቸው በልተው እኔ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ የሰበሰቡትንም የወይን ዘለላ የወይን ጠጅ እነርሱ ራሳቸው በተቀደሰ አደባባዬ ይጠጡታል።
የሆነ ሆኖ የሕዝቡ መሪ የተቀደሰውን የመሥዋዕት ኅብስት ለመብላት በዚያ መቀመጥ ይችላል፤ በመግቢያውም ክፍል ውስጠኛ ጫፍ በሚገኘው መተላለፊያ በኩል መግባትና መውጣት ይፈቀድለታል።”
ብዙ በልታችሁ ትጠግባላችሁ፤ ብዙ አስደናቂ ነገር ያደረግኹላችሁን እኔን እግዚአብሔር አምላካችሁን ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ኀፍረት አይደርስባቸውም።
በዚያም በመጀመሪያው ቀን ከምድራችሁ ዛፎች ምርጥ ፍሬ፥ የዘንባባ ዝንጣፊና የለምለም ዛፍ ቅርንጫፍ የወንዝ አኻያ ዛፍ ይዛችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት እየተደሰታችሁ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በዓል አድርጉ።
እናንተ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻችሁ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም ከእናንተ ጋር የርስት ክፍያ ከሌላቸው በከተሞቻችሁ ከሚኖሩ ከሌዋውያን ጋር በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትደሰታላችሁ።
አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጥልህ ቦታ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆችህ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮችህ፥ እንዲሁም በከተሞችህ ከሚኖሩ ሌዋውያን ጋር እነዚህን ትበላለህ፤ እዚያም በድካምህ ያገኘኸውን መልካም ነገር ሁሉ ትደሰትበታለህ፤
ሁልጊዜ አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራት ትማር ዘንድ ስሙ እንዲጠራበት በሚመርጠው ቦታ የእህልህን፥ የወይን ጠጅህን፥ የዘይትህን ዐሥራት፥ እንዲሁም የከብቶችህንና የበጎችህን በኲራት በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ትበላለህ፤
እዚያም በገንዘቡ የምተፈልገውን ነገር ከብት፥ ወይም በግ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ጠንካራ መጠጥ፥ ወይም ማንኛውንም የመረጥከውን ነገር ገዝተህ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አንተና ቤተሰብህ በመብላት ተደሰቱ።
ለአንተና ለቤተሰብህም እግዚአብሔር ባደረገላችሁ መልካም ነገር ሁሉ ደስ ብሎአችሁ አመስግኑ፤ ሌዋውያንና ከእናንተ ጋር የሚኖሩ መጻተኞች በዚህ የምስጋና ሥርዓት አፈጻጸም ላይ አብረው ይገኙ።