Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 12:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ያ ሰዓት በሚደርስበት ጊዜ እስከ አሁን እንደ ፈለጋችሁ በምትፈጽሙት ዐይነት አታደርጉም፤ እነሆ እስከ አሁን የመሰላችሁን ታደርጉ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዛሬ እንደምናደርገው ሁሉ፣ እያንዳንዱ የሚመስለውን እንዳደረገ አታድርጉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “ዛሬ እንደምናደርገው ሁሉ፥ እያንዳንዱ የሚመስለውን እንዳደረገ አታድርጉ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሰው ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን፥ እኛ በዚህ ዛሬ የም​ና​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ አታ​ድ​ርጉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን፥ እኛ በዚህ ዛሬ የምናደርገውን ሁሉ አታደርጉም፤

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 12:8
10 Referencias Cruzadas  

በዚያም ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ደስ ያለውን ነገር ሁሉ እንደ ፈለገ ያደርግ ነበር።


በዚያን ጊዜ በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ደስ ያለውን ነገር ሁሉ እንደ ፈለገ ያደርግ ነበር።


ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን የልብን ሐሳብ ይመዝናል።


እግዚአብሔር ግን ተለያቸው። የሰማይንም ከዋክብት እንዲያመልኩ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም በነቢያት እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፤ ‘እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ! የታረደውን እንስሳና መሥዋዕትን አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ያቀረባችሁት ለእኔ ነውን?


ዘርፎቹም እንደማስታወሻ ሆነው ስለሚያገለግሉ፥ እነርሱን በምታዩበት ጊዜ ሁሉ ትእዛዞቼን በማስታወስ ትፈጽማላችሁ፤ ከእኔም ርቃችሁ የገዛ ፈቃዳችሁንና ምኞታችሁን የምትፈጽሙ አትሆኑም፤


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በውኑ በአርባው ዓመት የምድረ በዳው ጒዞ ጊዜ መሥዋዕትና መባ አቅርባችሁልኛልን?


እዚያም በባረካችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ሁሉ ተሰብስባችሁ ትበላላችሁ፤ በድካማችሁ ያገኛችሁትን መልካም ነገር ሁሉ ትደሰቱበታላችሁ።


እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁና በሰላም ዕረፍት አድርጋችሁ ወደምትኖሩባት ርስት ገና አልገባችሁም፤


ከዚህ በኋላ ኢያሱ እስራኤላውያንን፦ “ወደዚህ ቅረቡና የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አድምጡ” አላቸው።


በመጀመሪያ ከግብጽ ምድር የወጡት ወንዶች ሁሉ ተገርዘው የነበሩ ቢሆኑም እንኳ በበረሓው ጒዞ ጊዜ የተወለዱት ወንዶች አልተገረዙም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios