1 ነገሥት 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “በፊቴ ያቀረብኸውን ጸሎትና ልመና ሰምቻለሁ፤ ይህን የሠራኸውንም ቤተ መቅደስ፣ ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ቀድሼዋለሁ፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አለው፥ “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ እንደ ጸሎትህም ሁሉ አደረግሁልህ፤ ለዘለዓለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዐይኖችና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አለው “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዐይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ። |
“ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤
በቤተ መቅደሱም ውስጥ የአሼራን ምስል አኖረ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እኔ ለዘለዓለም እመለክበት ዘንድ ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት ስፍራ ነው፤
በቤተ መቅደስም ውስጥ የጣዖት ምስልን አቆመ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ ስሜ እንዲጠራበት ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት የተቀደሰ ስፍራ ነው፤
ይህን ትእዛዝ ባለመቀበል በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለማፍረስ የሚሞክረውን ማንኛውንም ንጉሥ ወይም ሕዝብ የስሙ መጠሪያ ይሆን ዘንድ የመረጠ አምላክ ያስወግደው፤ ይህን ትእዛዝ ያስተላለፍኩ እኔ ዳርዮስ ስለ ሆንኩ በሙሉ መፈጸም አለበት።”
በስድስት ቀን እግዚአብሔር ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በእነርሱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቆመው ቢማልዱ ለዚህ ሕዝብ ምሕረት አላደርግም፤ ስለዚህ ከፊቴ ወዲያ እንዲሄዱ አድርግ።
ገና መጸለይ ስትጀምር እግዚአብሔር ልመናህን ሰምቶአል፤ አንተ በእርሱ ዘንድ የተወደድክ ስለ ሆነ የጸሎትህን መልስ ልነግርህ መጥቼአለሁ፤ እንግዲህ የምነግርህን አዳምጠህ የራእዩን ትርጒም ተረዳ።
ጥናዎቹም የተቀደሱት ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ በቀረቡ ጊዜ ነው፤ ስለዚህ በኃጢአታቸው የተገደሉትን የእነዚህን ሰዎች ጥናዎች ውሰድና በመቀጥቀጥ እንዲሳሱ አድርግ፤ ለመሠዊያውም መክደኛ እንዲሆኑ አድርገህ ሥራቸው፤ ለእስራኤል ሕዝብ የመቀጣጫ ማስጠንቀቂያ ይሆናል።”
ከዚያም እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ የምታመጡት እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ መጠሪያ ወደ መረጠው ቦታ ይሆናል፤ ይኸውም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትን የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን ሁሉ ታመጡለታላችሁ።
እግዚአብሔር የመረጠው ያ አንድ ስፍራ ሩቅ ቢሆንብህ ግን በሚያሰኝህ ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ከሰጠህ የከብትም ሆነ የበግ መንጋ መርጠህ እኔ ባዘዝኩህ መሠረት ማረድ ትችላለህ፤ ሥጋውንም በቤት ትበላዋለህ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤
ከወንዶችና ከሴቶች ልጆችህ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮችህ በከተሞችህ ከሚኖሩት ሌዋውያን፥ በአገርህ የሚኖሩ መጻተኞች፥ እናትና አባት ከሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ሴቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት እርሱ ለስሙ መጠሪያ እንዲሆን በመረጠው ቦታ በአንድነት ተሰብስበህ ደስ ይበልህ።