Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 34:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የጌታ ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ተነሥቶአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ትፈ​ር​ድ​ል​ኛ​ለህ? ነፍ​ሴን ከክፉ ሥራ​ቸው፥ ብቸ​ኝ​ነ​ቴ​ንም ከአ​ን​በ​ሶች አድ​ናት፥

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 34:17
17 Referencias Cruzadas  

በዚያኑ ጊዜ ንጉሥ ሕዝቅያስ ታሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ እግዚአብሔርም እንደሚያድነው የሚያረጋግጥ ምልክት አሳየው።


“እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን አይጥላቸውም፤ ክፉዎችንም አይረዳቸውም።


እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ዘወትር ያስታውስ፤ እነርሱ ራሳቸው ግን ፈጽሞ የተረሱ ይሁኑ።


እግዚአብሔር ወደ ጻድቃን ይመለከታል፤ ጸሎታቸውንም ያደምጣል።


ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል።


ይህ ድኻ ሰው ተጣራ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከችግሩም ሁሉ አዳነው።


እኔ ግን በታላቅ ምሕረትህ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ወደ ቤተ መቅደስህ በአክብሮት እሰግዳለሁ።


ጠላቶቻችን ለዘለዓለም ጠፍተዋል፤ ከተሞቻቸውንም ደምስሰሃል፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል።


በሚጠራኝም ጊዜ እሰማዋለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁም።


የጻድቅ ሰው መታሰቢያ ለበረከት ይሆናል የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል።


እኔን በልመና ከመጥራታቸው በፊት እመልስላቸዋለሁ፤ እየጸለዩም ሳለ እሰማቸዋለሁ።


እኔም በእርሱ ላይ አተኲሬ መቀጣጫና መዘባበቻ አደርገዋለሁ ከሕዝቤ መካከል አስወግደዋለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


በጠላቶቻቸው እጅ ተማርከው ቢወሰዱም እዚያ እንዲገደሉ አደርጋለሁ፤ በዚህ ዐይነት እኔ በእነርሱ ላይ የማደርገው ትኲረት ይጐዳቸዋል እንጂ አይጠቅማቸውም።”


እኔ ፈጽሜ እደመስሳቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos