19 አሁን ግን በእርግጥ እግዚአብሔር ሰምቶኛል፤ የልመናዬንም ድምፅ አድምጦአል።
19 አሁን ግን እግዚአብሔር በርግጥ ሰምቶኛል፤ ጸሎቴንም አድምጧል።
19 ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ፥ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ።
“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።
ይህ ድኻ ሰው ተጣራ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከችግሩም ሁሉ አዳነው።
እግዚአብሔር ልመናዬን ያዳምጣል፤ እግዚአብሔር ለጸሎቴ መልስ ይሰጣል።
ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።