1 ነገሥት 21:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል” ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሁለት ምናምንቴ ሰዎች መጥተው ከፊት ለፊቱ ተቀመጡ፤ በሕዝቡም ፊት፣ “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቧል” ብለው መሰከሩበት። ስለዚህ ከከተማዪቱ ውጭ ወስደው በድንጋይ ወግረው ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እንግዲህ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ አለ። |
ወዲያውኑም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ ሊጐበኙት ከመጡ ጥቂት ሽማግሌዎች ጋር በቤት ውስጥ ነበር፤ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን “ያ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ፥ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል” አላቸው።
‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ።
ንጉሥ ኢዮአስ በዘካርያስ ላይ በተደረገው ሤራ ተባባሪ ሆነ፤ ሕዝቡም በንጉሡ ትእዛዝ ዘካርያስን በቤተ መቅደሱ አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
የግብዣዎቹ ቀኖች ከተፈጸሙ በኋላ ኢዮብ በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹን ያስጠራና በእያንዳንዱ ልጁ ስም መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ ይህንንም የሚያደርገው “ምናልባት ከልጆቼ አንዱ እግዚአብሔርን በመስደብ በድሎ ይሆናል!” በሚል ስጋት ልጆቹን ከኃጢአት ለማንጻት ነበር። ኢዮብ ይህን ሥርዓት ሳያቋርጥ ዘወትር ይፈጽም ነበር።
የሚሰማብኝ የለም ብለህ በስውር እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትማ፤ በተኛህበት አልጋህ ላይ ሆነህም ባለጸጋን አትስደብ፤ ምሥጢርህን የሰሙ ነገር ጠላፊዎች ክንፍ እንዳለው ወፍ በረው ሊነግሩብህ ይችላሉ።
እንደገናም በዓለም ያለውን የፍርድ መጓደልና ግፍ ተመለከትኩ፤ የተገፉ ጭቊኖች የሚያጽናናቸው አጥተው ያለቅሱ ነበር፤ የፈላጭ ቈራጭነት ሥልጣን በገዢዎቻቸው እጅ ስለ ሆነ የሚረዳቸው አላገኙም።
ሕዝቡ ተስፋ ቈርጠውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ከመራባቸው የተነሣ ተበሳጭተው ወደ ሰማይ እያንጋጠጡ ንጉሣቸውንና አማልክታቸውን ይራገማሉ።
የቤትኤል ካህን የሆነው አሜስያስ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም ላከ፦ “እነሆ አሞጽ በእስራኤል ሕዝብ መካከል ሆኖ በአንተ ላይ እያሤረብህ ነው፤ ሕዝቡ የእርሱን ንግግር ሊታገሥ አይችልም።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።
እንዲህ እያሉም ይከሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት አገኘነው፤ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር እንዳይከፈል ይከለክላል፤ ደግሞ ‘እኔ ንጉሥ መሲሕ ነኝ’ እያለ ይናገራል።”
ጲላጦስ ይህን የኢየሱስን አነጋገር በሰማ ጊዜ ፈቶ ሊለቀው ፈልጎ ነበር፤ አይሁድ ግን “ይህን ሰው ከፈታኸው አንተ የሮም ንጉሠ ነገሥት ወዳጅ አይደለህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሁሉ የንጉሠ ነገሥቱ ጠላት ነው!” እያሉ ጮኹ።
የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ወግረው ይግደሉት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ታስወግዳላችሁ፤ በእስራኤልም የሚኖር ሁሉ ይህን ሁኔታ ሰምቶ ይፈራል።
በአባትዋ ቤት እያለች አሳፋሪ የሆነውን የዝሙት ሥራ በእስራኤል መካከል ስለ ሠራች ወደ አባትዋ ቤት ደጃፍ ይውሰዱአት፤ በዚያም እርስዋ የምትኖርበት ከተማ ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።
ሁለቱንም ከከተማይቱ ወደ ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉ፤ ልጃገረዲቱ መሞት የሚገባት ሰው ሊሰማ በሚችልበት ከተማ ውስጥ እያለች ርዳታ እንዲደረግላት የጩኸት ድምፅ ባለማሰማትዋ ነው፤ ሰውየውም የሚሞትበት ምክንያት ለሌላ ሰው ከታጨች ልጃገረድ ጋር በመተኛት ሕግን በማፍረሱ ነው፤ በዚህ ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።