Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 22:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በአባትዋ ቤት እያለች አሳፋሪ የሆነውን የዝሙት ሥራ በእስራኤል መካከል ስለ ሠራች ወደ አባትዋ ቤት ደጃፍ ይውሰዱአት፤ በዚያም እርስዋ የምትኖርበት ከተማ ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ገና በአባቷ ቤት ሳለች በማመንዘር በእስራኤል ውስጥ ወራዳ ተግባር ፈጽማለችና ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያምጧት፤ እዚያም የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት። ክፉውን ከመካከልህ ማስወገድ አለብህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩአት፥ ይህን በማድረግም ክፉውን ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያው​ጡ​አት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስን​ፍ​ናን አድ​ር​ጋ​ለ​ችና፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤት አስ​ነ​ው​ራ​ለ​ችና የከ​ተ​ማው ሰዎች በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 22:21
24 Referencias Cruzadas  

በባርነት ከኖራችሁባት ከግብጽ ምድር ነጻ በማውጣት በአዳናችሁ በእግዚአብሔር ላይ እንድታምፁ የሚያደርጋችሁን ሕልም አላሚ ወይም ነቢይ ነኝ ባዩን ሁሉ ግደሉ፤ እንደዚህ ያለው ሰው ጸንታችሁ እንድትኖሩበት እግዚአብሔር አምላካችሁ ካዘዛችሁ መንገድ ሊለያችሁ ያቀደ ነው፤ ስለዚህ እናንተ ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።


ልክ በዚያኑ ጊዜ የያዕቆብ ልጆች ከተሰማሩበት መጡ፤ ስለ ተፈጸመው ድርጊት በሰሙ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፤ ይህ ነገር መደረግ ስላልነበረበት ሴኬም የያዕቆብን ልጅ በመድፈር የእስራኤልን ሕዝብ በማዋረዱም እጅግ ተቈጡ።


ከዚህ በኋላ የቁባቴን አስከሬን ወስጄ ቈራረጥሁት፤ እነርሱ ይህን የመሰለ ክፉ በደል ስለ ሠሩ የቈራረጥኋቸውን ቊርጥራጮች ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ላክሁ።


በእስራኤል ላይ በፈጸሙት አሳፋሪ ተግባር በብንያም ግዛት የምትገኘውን የጊብዓን ሕዝብ ለመበቀል ለሚዘምተው ሠራዊት ስንቅ ያቀብሉ ዘንድ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ከመቶ ዐሥር፥ ከሺህ መቶ፥ ከዐሥር ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንመድባለን።”


የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ወግረው ይግደሉት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ታስወግዳላችሁ፤ በእስራኤልም የሚኖር ሁሉ ይህን ሁኔታ ሰምቶ ይፈራል።


ለተከሳሹ ታስቦ የነበረውን ቅጣት እርሱ ይቀበላል፤ ይህን የመሰለ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ዐይነት ታስወግዳለህ።


ምስክሮቹ የመጀመሪያዎቹን ድንጋዮች ይወርውሩ፤ ከዚያም ቀጥሎ ሌላው ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው፤ በዚህም ዐይነት እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ሁሉ ከመካከልህ ታስወግዳለህ።


የማንኛውም ካህን ሴት ልጅ አመንዝራ ብትሆን አባትዋን ታስነውራለች፤ እርስዋ በእሳት ተቃጥላ ትሙት።


ሁለቱንም ከከተማይቱ ወደ ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉ፤ ልጃገረዲቱ መሞት የሚገባት ሰው ሊሰማ በሚችልበት ከተማ ውስጥ እያለች ርዳታ እንዲደረግላት የጩኸት ድምፅ ባለማሰማትዋ ነው፤ ሰውየውም የሚሞትበት ምክንያት ለሌላ ሰው ከታጨች ልጃገረድ ጋር በመተኛት ሕግን በማፍረሱ ነው፤ በዚህ ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።


“አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ሁለቱም ይገደሉ። በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከእስራኤል አስወግዱ።


ያን ሰው ወይም ያቺን ሴት ከከተማ ወደ ውጪ አውጥተህ በድንጋይ ወግረህ ግደል።


በባርነት ከኖርክበት ከግብጽ ምድር ነጻ ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ስለ ሞከረ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው፤


ሙሴም ይህን ሁሉ ለሕዝቡ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ ያን ሰው ከሰፈር አወጡና በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህም ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።


የእግዚአብሔርን ስም የሚሰድብ ይገደል፤ ማኅበረሰቡ ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት፤ እስራኤላዊም ሆነ መጻተኛ የእግዚአብሔርን ስም ሲሰድብ ይገደል።


በውጪ ስላሉት ሰዎች ጉዳይ የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፤ እንግዲህ መጽሐፍ እንደሚል “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱ።”


“ምድሪቱ በዝሙትና በርኲሰት እንዳትሞላ ታመነዝር ዘንድ ለሴት ልጅህ አትፍቀድላት።


ሽማግሌው ግን ወደ ውጪ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “አይሆንም ወዳጆቼ ሆይ! እባካችሁ ይህን የመሰለ አስከፊ ነገር አታድርጉ! ይህ ሰው የእኔ እንግዳ ነው፤


የጊብዓ ሰዎች በእኔ ላይ አደጋ ለመጣል መጥተው በሌሊት ቤቱን ከበቡት፤ በመጀመሪያ እኔን ለመግደል አስበው ነበር፤ በኋላ ግን በቊባቴ ላይ ተረባርበው ስላመነዘሩባት ሞተች፤


በሦስተኛው ወር ገደማ ሰዎች “ምራትህ ትዕማር የዝሙት ሥራ ፈጸመች፤ ከዚህም የተነሣ ፀንሳለች” ብለው ለይሁዳ ነገሩት። ይሁዳም “ወደ ውጪ አውጥታችሁ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉአት” አለ።


“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገር፦ ከእናንተም ሆነ ወይም በመካከላችሁ ከሚኖሩት የውጪ አገር ተወላጆች ውስጥ፥ ማንም ሰው ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ ከልጆቹ አንዱን አሳልፎ ሰጥቶ ቢገኝ መላው የእስራኤል ሕዝብ በድንጋይ ወግሮ ይግደለው።


“በቅርብም ሆነ በሩቅ ካሉት፥ ከአንዱ የምድር ዳርቻ በአካባቢህ ካሉ ከአሕዛብ አማልክት አንተ ወይም አባቶችህ የማታውቁትን አንዱን እናምልክ በማለት ሌላ እንኳ ቀርቶ የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ በምሥጢር ይገፋፋህ ይሆናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios