1 ዮሐንስ 1:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሕይወት ተገልጦአል፤ እኛም አይተነዋል፤ እንመሰክራለንም። በአብ ዘንድ የነበረውንና ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለም ሕይወት እንነግራችኋለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ሕይወት ተገለጠ፤ እኛም አይተናል፤ እንመሰክራለንም። ከአብ ዘንድ የነበረውን፣ ለእኛም የተገለጠውን የዘላለም ሕይወት እንነግራችኋለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕይወትም ተገለጠ፥ አይተነዋል እንመሰክራለንም፥ በአብ ዘንድ የነበረውን ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ |
እንዲሁም ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ አብረውን ከነበሩት ከነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”
የተገለጠውም አስቀድሞ በእግዚአብሔር ለተመረጡት ምስክሮች ነው እንጂ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፤ እርሱ ከሞት ከተነሣ በኋላ እኛ ከእርሱ ጋር አብረን የበላንና የጠጣን ምስክሮቹ ነን፤
ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።
ይህም ጸጋ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣቱ አሁን ተገለጠ። እርሱ የሞትን ኀይል ደምስሶ በወንጌል አማካይነት ሞት የሌለበትን ዘለዓለማዊ ሕይወት ገለጠልን።
እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር አብሬ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ የሆንኩ፥ የክርስቶስም መከራ ምስክር የሆንኩ፥ እንዲሁም ወደፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን፥ በመካከላችሁ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ።
ከመጀመሪያው ስለ ነበረው ስለ ሕይወት ቃል እንጽፍላችኋለን፤ ይህ የሕይወት ቃል የሰማነውና በዐይኖቻችን ያየነው፥ የተመለከትነውና በእጆቻችን የዳሰስነው ነው።
ዲያብሎስ ከመጀመሪያው አንሥቶ ኃጢአት ስለሚሠራ ኃጢአትን የሚሠራ ሁሉ የዲያብሎስ ወገን ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው።
የእግዚአብሔርን መንፈስ ለይታችሁ የምታውቁት በዚህ ነው፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡን የሚያምን መንፈስ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፤
የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።