Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 1:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እንዲሁም ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ አብረውን ከነበሩት ከነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይኸውም፣ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ኢየሱስ ከእኛ ተለይቶ እስካረገበት ቀን ድረስ የነበረ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋራ የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእኛ መካ​ከል በገ​ባ​በ​ትና በወ​ጣ​በት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብ​ረው ከነ​በ​ሩት ከእ​ነ​ዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የት​ን​ሣ​ኤዉ ምስ​ክር ይሆን ዘንድ ይገ​ባል።”

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 1:22
16 Referencias Cruzadas  

ወደ ሰማይ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ የሠራውን ነው፤ ወደ ሰማይ ያረገውም ለመረጣቸው ሐዋርያት ትእዛዙን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከሰጣቸው በኋላ ነው፤


ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስን ትንሣኤ በታላቅ ኀይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ ነበረ።


ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


እናንተም ከመጀመሪያ አንሥቶ ከእኔ ጋር ስለ ነበራችሁ ትመሰክራላችሁ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በገሊላ ክፍለ ሀገር ከምትገኝ ከናዝሬት ከተማ መጥቶ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ።


ጌታ ኢየሱስ ይህን ሁሉ ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ። በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስም ተጠመቀ፤ እርሱ ሲጸልይ ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤


እናንተም የዚህ ሁሉ ነገር ምስክሮች ናችሁ፤


“እናንተ የገሊላ ሰዎች፥ ስለምን ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ቆማችኋል? ይህ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፥ ወደ ሰማይ ሲያርግ ባያችሁት ዐይነት ተመልሶ ይመጣል” አሉአቸው።


ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር ከሞት አስነሣው፤ እኛም ሁላችን ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios