ኢዮብ 17:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መበስበስን፦ አንተ አባቴ ነህ፥ ትልንም፦ አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መበስበስን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ ትልንም፣ ‘አንቺ እናቴ’ ወይም ‘እኅቴ ነሽ’ ካልሁ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቃብርን ‘አባቴ’ ብዬ እጠራዋለሁ፤ የሚበሉኝንም ትሎች ‘እናቴና እኅቴ’ እላቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞትን፦ አንተ አባቴ ነህ አልሁት፤ ትሎችንም እናንተ እናቴም ወንድሞቼም ናችሁ አልኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መበስበስን፦ አንተ አባቴ ነህ፥ ትልንም፦ አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ። |