Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።

2 አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ፥ በዓለም የምትኖሩትም ሁላችሁ፥ አድምጡ፥

3 ዝቅተኞችና ከፍተኞች፥ ሀብታሞችና ድሆች በአንድነት።

4 አፌ ጥበብን ይናገራል፥ የልቤም አስተንትኖ ማስተዋልን።

5 ጆሮዬን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፥ በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ።

6 በደል ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?

7 በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በሀብታቸውም ብዛት የሚመኩ፥

8 በእውነት ማንም እራሱን አያድንም፥ ማንም ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥

9 የነፍሳቸው ዋጋ ክቡር ነው፥ መቼውንም በቂ አይሆንም፥

10 ሰው ገና እንዲኖርና አዘቅቱንም እንዳያይ

11 ጠቢባን እንደሚሞቱ፥ ሰነፎችና ደንቆሮች በአንድነት እንደሚጠፉ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንደሚተዉ አይቶአል።

12 ብዙ መሬት በስማችው ቢያስጠሩም እንኳን፥ መቃብራቸው የዘለዓለም ቤታቸው፥ ለልጅ ልጅ የሚሆን ማደሪያቸውም ነው።

13 ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፥ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።

14 ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በንግግራቸው ይደሰታሉ።

15 እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚሄዱ ናቸው፥ እረኛቸውም ሞት ነው፥ ቅኖችም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ውበታቸውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች።

16 ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል።

17 የሰው ሀብት የቤቱም ክብር በበዛ ጊዜ አትፍራ፥

18 በሞተ ጊዜ ከእርሱ ጋር ምንም አይወስድምና፥ ክብሩም ከእርሱ በኋላ አይወርድምና።

19 በሕይወቱ ሳለ ነፍሱን ባርኮአልና ለሰውነቱ መልካም በማድረጉ ይወደሳልና።

20 ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል፥ ለዘለዓለም ብርሃንን ወደ ማያዩበት።

21 አእምሮ የሌለው ክቡር ሰው እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos