1  ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦ 
 2  “ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ በከፍታውም ሰላምን የሚያሰፍን ነው። 
 3  በውኑ ለሠራዊቱ ቍጥር ስፍር አለውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው? 
 4  ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፥ ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል? 
 5  እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን ካልሆኑ። 
 6  ይልቁንስ ፈራሽ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!”