ስለዚህ ሐኑን የዳዊትን አገልጋዮች ይዞ፥ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፥ ልብሳቸውንም ወገባቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ሰደዳቸው።
ኢሳይያስ 15:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቷል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጺቦን ሕዝብም በቤተ ጣዖታቸው ለማልቀስ ወደ ኰረብታ ይወጣሉ፤ የሞአብ ሕዝብ ስለ ነቦና ስለ ሜዳባ ከተሞቻቸው በከባድ ሐዘን ያለቅሳሉ፤ ከሐዘናቸውም የተነሣ ጠጒራቸውንና ጢማቸውን ተላጭተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፥ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፥ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቶአል። |
ስለዚህ ሐኑን የዳዊትን አገልጋዮች ይዞ፥ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፥ ልብሳቸውንም ወገባቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ሰደዳቸው።
አንተ በር ሆይ፥ ወዮ በል፥ አንቺም ከተማ ሆይ፥ ጩኺ፤ ፍልስጥኤም ሆይ፥ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይመጣል ከጭፍራውም ተለይቶ የሚቀር የለም።
“ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ጐርፍ ይሆናል፤ በአገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።
ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች ተይዛለችም፤ አምባይቱም አፍራለች ፈርሳለችም።
ሐሴቦን ሆይ! ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺ፤ እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ! ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፥ ማቅም ታጠቁ፥ አልቅሱም፥ በቅጥሮችም መካከል ተርዋርዋጡ።
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬአችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ፥ ጸጉር መላጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ፥ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።