Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ኤርምያስ 47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ፍልስጥኤም ላይ የተደረገ ፍርድ

1 ፈርዖንም ጋዛን ከመምታቱ በፊት ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው።

2 “ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ጐርፍ ይሆናል፤ በአገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።

3 ከኃይለኞች ፈረሶቹ የኮቴያቸው ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መንጐድ፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ወደ ልጆቻቸው ዘወር ብለው አይመለከቱም።

4 ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለመደምሰስ የተረፉትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ለማጥፋት ስለሚመጣው ቀን ነው፤ ጌታ ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ትሩፍ ያጠፋልና።

5 ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቷል፤ አስቀሎና በጸጥታ ተውጣለች፤ በሸለቆ ያላችሁ ትሩፋን ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላችሁን ትተለትላላችሁ?

6 አንተ የጌታ ሰይፍ ሆይ! ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ግባ ጸጥ ብለህም ዕረፍ።

7 ጌታ ትእዛዝ ሰጥቶት እንዴት ዝም ይላል? በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ በዚያ አዘጋጅቶታል።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos