Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘዳግም 34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የሙሴ አሟሟት

1 ሙሴም ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፒስጋ ራስ ወጣ፥ ጌታም እስከ ዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር፥

2 የንፍታሌምንም ምድር ሁሉ፥ የኤፍሬምንና የምናሴንም ምድር፥ እስከ ምዕራብም ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ፥ ደቡቡንም፥

3 እስከ ጾዓር ድረስ ያለውንም የዘንባባ ዛፎች ያሉባትን ከተማ የኢያሪኮን ሸለቆ ሜዳ አሳየው።

4 ጌታም፦ “ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት፥ በዓይንህ እንድታያት አደረግሁህ፥ ነገር ግን ወደዚያች አትሻገርም” አለው።

5 የጌታ ባርያም ሙሴ እንደ ጌታ ቃል በሞዓብ ምድር ሞተ።

6 በቤተ ፌጎርም ፊት ለፊት በሞዓብ ምድር በሸለቆው ውስጥ ተቀበረ፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩን ማንም አላወቀም።

7 ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ዓመት ነበረ፥ ዓይኑ አልፈዘዘም፥ ጉልበቱም አልደነገዘም።

8 የእስራኤልም ሕዝብ የሐዘኑ ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ ለሙሴ በማዘንሠላሳ ቀን በሞዓብ ሜዳ አለቀሱለት።

9 ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ፤ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፤ ሙሴንም ጌታ እንዳዘዘው አደረጉ።

10 ጌታን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም።

11 በግብጽ ምድር በፈርዖንና በባርያዎቹ ሁሉ ላይ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን እንዲያደርግ ጌታ የላከው፥

12 እንደ ሙሴ በእስራኤል ሁሉ ፊት ያሳየውን የጸና ክንድ ያሳየ ወይም ያደረገውን አስፈሪ ነገር የፈጸመ ማንም የለም።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos