ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ ጌታ እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።
ሆሴዕ 10:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልባቸው ሐሰተኛ ነው፤ በደላቸውን አሁን ይሸከማሉ፤ ጌታ መሠዊያዎቻቸውን ይሰባብራል፥ ሐውልቶቻቸውን ያጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባቸው አታላይ ነው፤ ስለዚህም በደላቸውን ይሸከማሉ። እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ያወድማል፤ የጣዖት ማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ያፈራርሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልባቸው በተንኰል የተሞላ ነው፤ የበደላቸውንም ዋጋ ያገኛሉ፤ እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ሁሉ ይሰባብራል፤ የጣዖት መስገጃ ዐምዶቻቸውንም ያፈራርሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባቸው ተከፈለ፤ አሁንም ይጠፋሉ፤ እርሱ መሠዊያቸውን ያፈርሳል፤ ሐውልቶቻቸውንም ያጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልባቸው ተከፈለ፥ አሁንም በደላቸውን ይሸከማሉ፥ እርሱ መሠዊያቸውን ያፈርሳል፥ ሐውልቶቻቸውን ያጠፋል። |
ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ ጌታ እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።
የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።
በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ የጣዖታትን ስም ከምድር አጠፋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አይታሰቡም፤ ደግሞም ሐሰተኞችን ነቢያትና ርኩስ መንፈስን ከምድር ላይ አስወግዳለሁ።
“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”
ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው አንድም አገልጋይ የለም፤ ወይ አንዱን ሲጠላ ሌላውን ይወዳል፤ ወይ አንዱን ሲጠጋ ሌላውን ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”
አመንዝሮች ሆይ! ከዓለም ጋር ወዳጅ መሆን የእግዚአብሔር ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።
ነገር ግን በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ተነሥተው ሲመለከቱ፥ ዳጎን በጌታ ታቦት ፊት፥ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ነበር፤ ራሱና እጆቹ ተሰባብረው በደጃፉ ላይ የወደቁ ሲሆኑ፥ የቀረው ሌላው አካሉ ብቻ ነበር።