Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 23:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ለአማልክቶቻቸው አትስገድ፥ አታገልግላቸውም፥ እንደ ሥራቸውም አትሥራ፤ ነገር ግን ፈጽመህ አፍርሳቸው፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብራቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ለአማልክታቸው አትስገድ፤ ወይም አታምልካቸው፤ ወይም ልምዳቸውን አትከተል፤ እነርሱን ማፈራረስ አለብህ፤ የአምልኮ ድንጋዮቻቸውንም ሰባብር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ለእነርሱ አማልክት በመንበርከክ አትስገድ፤ አታምልካቸው፤ ሃይማኖታዊ ልማዶቻቸውንም አትከተል፤ አማልክታቸውን አጥፋ፤ ለእነርሱ ቅዱሳን የሆኑትን የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም አፈራርስ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው አት​ስ​ገድ፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም አት​ሥራ፤ ነገር ግን ፈጽ​መህ አፍ​ር​ሳ​ቸው፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ለአማልክቶቻቸው አትስገድ፥ አታምልካቸውም፤ እንደ ሥራቸውም አትሥራ፤ ነገር ግን ፈጽመህ አፍርሳቸው፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብራቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 23:24
29 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ከምድሪቱ ነቃቅሎ ያስወጣቸውን የአረማውያንን ሕዝብ ልማድ በመከተል በአሕዛብ መሠዊያዎች ሁሉ ላይ ዕጣን አጠኑ፤ በዚህም ክፉ ሥራቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፤


ሕዝቡ ወደ ፊት እየገፋ በመጣ ጊዜ ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸውን የአሕዛብን መጥፎ ልማድ ተከተሉ፤ እንዲሁም የእስራኤል ነገሥታት ያሠራጩትን መጥፎ ልማድ ተቀባዮች ሆኑ።


የአሕዛብን የማምለኪያ ስፍራዎችን ደመሰሰ፤ የድንጋይ ዐምዶችን ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ በምትጠራው ሴት አምላክ ስም የተቀረጹትን ምስሎች ሁሉ አንኮታክቶ ጣለ፤ ሙሴ ከነሐስ ሠርቶት የነበረውን ኔሑሽታን ተብሎ የሚጠራውን የእባብ ምስል ሰባብሮ አደቀቀ፤ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ግን እስራኤላውያን ለእርሱ ዕጣን ያጥኑለት ነበር።


እርሱም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ ይሁን እንጂ እርሱ የአባቱንና የእናቱን የኤልዛቤልን ያኽል መጥፎ ሰው አልነበረም፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውን ባዕድ አምላክ ለማምለክ አባቱ አሠርቶት የነበረውን ምስል አስወገደ፤


አሳም በአምላኩ በጌታ ፊት መልካምና ቅን ነገር አደረገ፤


አሜስያስም የኤዶማውያንን ሰዎች ከገደለ በኋላ የሴይርን ልጆች አማልክት አመጣ፥ የእርሱም አማልክት እንዲሆኑ አቆማቸው፥ ይሰግድላቸውም ያጥንላቸውም ነበር።


ጌታም ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳወጣቸው እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት በጌታ ፊት ክፉ ነገር አደረገ።


ምናሴም ጌታ ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ እንዲሠሩ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ።


በዓይኔ ፊት ክፉን ነገር አላኖርሁም፥ ሕግ ተላላፊዎችን ጠላሁ።


“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።


አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥


የነገርኳችሁን ነገር ሁሉ ጠብቁ፤ የሌሎችን አማልክት ስም አትጥሩ፥ ከአፍህም አይሰማ።


ከእነርሱ ጋርና ከአማልክቶቻቸው ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ።


በምድርህ አይቀመጡ አማልክቶቻቸውን በማገልገል እኔን እንድትበድል ያደርጉሃልና፥ ይህም ለአንተ ወጥመድ ይሆንብሃል።”


የሠሩትን ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እስኪደቅም ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲጠጡት አደረገ።


አንቺ በእነርሱ መንገድ መሄድሽና ርኩሰታቸውንም መከተልሽ ብቻ ሳይሆን፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመንገድሽ ሁሉ ከእነርሱ የበለጠ ምግባረ ብልሹ ነበርሽ።


ልባቸው ሐሰተኛ ነው፤ በደላቸውን አሁን ይሸከማሉ፤ ጌታ መሠዊያዎቻቸውን ይሰባብራል፥ ሐውልቶቻቸውን ያጠፋል።


በተቀመጣችሁባት በግብጽ ምድር እንደሚያደርጉት እናንተም እንዲሁ አታድርጉ፤ እኔም ወደማመጣችሁ ስፍራ ወደ ሆነው በከነዓን ምድር ላይ እንደሚያደርጉት እናንተም እንዲሁ አታድርጉ፤ በሥርዓታቸውም አትሂዱ።


“እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና ለራሳችሁ ይሆኑ ዘንድ ጣዖታትን አትሥሩ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ለእርሱም ለመስገድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።


ሕዝቡንም ወደ አማልክቶቻቸው መሥዋዕት ጠሩ፤ ሕዝቡም በሉ፥ ለአማልክቶቻም ሰገዱ።


የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤


መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፤ የማምለኪያ አምዶቻቸውን ሰባብሩ፤ የ ‘አሼራ’ ምስል ዐምዶቻቸውን በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን ጣዖቶች ቆራርጣችሁ ጣሉ፤ ስማቸውንም ከእነዚያ ስፍራዎች ላይ አጥፉ።”


ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም አድቅቁት፥ የእነርሱንም አሼራ ሰባብሩ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos