Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 10:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ልባቸው በተንኰል የተሞላ ነው፤ የበደላቸውንም ዋጋ ያገኛሉ፤ እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ሁሉ ይሰባብራል፤ የጣዖት መስገጃ ዐምዶቻቸውንም ያፈራርሳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ልባቸው አታላይ ነው፤ ስለዚህም በደላቸውን ይሸከማሉ። እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ያወድማል፤ የጣዖት ማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ያፈራርሳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ልባቸው ሐሰተኛ ነው፤ በደላቸውን አሁን ይሸከማሉ፤ ጌታ መሠዊያዎቻቸውን ይሰባብራል፥ ሐውልቶቻቸውን ያጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ልባ​ቸው ተከ​ፈለ፤ አሁ​ንም ይጠ​ፋሉ፤ እርሱ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን ያፈ​ር​ሳል፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያጠ​ፋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ልባቸው ተከፈለ፥ አሁንም በደላቸውን ይሸከማሉ፥ እርሱ መሠዊያቸውን ያፈርሳል፥ ሐውልቶቻቸውን ያጠፋል።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 10:2
24 Referencias Cruzadas  

ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።


ለእነርሱ አማልክት በመንበርከክ አትስገድ፤ አታምልካቸው፤ ሃይማኖታዊ ልማዶቻቸውንም አትከተል፤ አማልክታቸውን አጥፋ፤ ለእነርሱ ቅዱሳን የሆኑትን የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም አፈራርስ፤


ክፉ ሰዎች የሚያገኙት ጥቅም አይኖርም፤ ትክክል የሆነውን ነገር ብታደርግ፥ የመልካም ሥራህን ዋጋ ታገኛለህ።


እንደዚህ ያሉት ሰዎች ዐይኖቻቸው ስለ ተሸፈኑ ማየት አይችሉም።


በግብጽ ውስጥ በሄሊዮፖሊስ ከተማ የሚገኙትን ከድንጋይ የተሠሩ ሐውልቶችን ይደመስሳል፤ የግብጻውያንን ጣዖቶችንና ቤተ መቅደሶችን ያቃጥላል።”


ይህን የማደርገው እኔን ትተው ወደ ጣዖቶቻቸው በመሄድ ከእኔ ተለይተው የነበሩትን የእስራኤላውያንን ሁሉ ልብ ለመመለስ ነው።


ይህም ሁሉ ሆኖ በገለዓድ ለጣዖት ይሰግዳሉ፤ ለጣዖት የሚሰግዱት ግን ከንቱ ይሆናሉ፤ በጌልገላ ወይፈኖችን ለመሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ነገር ግን መሠዊያዎቻቸው ተሰባብረው በእርሻ መካከል የድንጋይ ክምር ሆነው ይቀራሉ።”


ሰማርያ በእኔ ላይ በማመፅዋ በሠራችው በደል ተጠያቂ ትሆናለች፤ ሕዝብዋም በጦርነት ይሞታሉ፤ ሕፃናት በምድር ላይ ይፈጠፈጣሉ፤ እርጉዞችም ሆዳቸው ይሰነጠቃል።”


በዚሁ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ ወይም ያለ መሪ፥ ያለ መሥዋዕት ወይም ያለ ሐውልት፥ ያለ ልብሰ ተክህኖ ወይም የጣዖት ምስል ለብዙ ዘመን ይኖራሉ፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ከአሕዛብ ጋር ተደባለቁ፤ በዚህም ምክንያት እነርሱ እንዳልተገለበጠ ቂጣ የማይጠቅሙ ሆነዋል፤


በየኰረብታው ላይ ያሉአችሁን መስገጃዎች እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈራርሳለሁ፤ ሬሳዎቻችሁንም በወደቁት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ፈጽሞ እጸየፋችኋለሁ፤


የተቀረጹ ጣዖቶቻችሁንና የምትሰግዱላቸው ዐምዶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ የእጆቻችሁ ሥራ ለሆኑ ጣዖቶች ከእንግዲህ ወዲህ አትሰግዱም።


ጣራ ላይ ወጥተው ለፀሐይ፥ ለጨረቃና ለከዋክብት የሚሰግዱትን አጠፋለሁ፤ እኔን እያመለኩና በስሜ እየማሉ፥ ዘወር ብለው ደግሞ ሚልኮም ተብሎ በሚጠራው ጣዖት ስም የሚምሉትን እደመስሳለሁ።


በዚያን ጊዜ የጣዖቶችን ስሞች ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ፤ ዳግመኛም የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ የጣዖት ነቢያትንና ርኩሳን መናፍስትን አስወግዳለሁ።


“አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች አገልጋይ ሊሆን አይችልም፤ ወይም አንዱን ይጠላል፥ ሌላውንም ይወዳል፤ ወይም አንዱን ያከብራል፥ ሌላውን ይንቃል፤ እንዲሁም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ አገልጋይ መሆን አይችልም።


“አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለሁለት ጌታ ማገልገል አይችልም፤ ይህ ከሆነ፥ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ አንዱን አክብሮ፥ ሌላውን ይንቃል፤ እንዲሁም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ ልትገዙ አትችሉም።”


ይህም የሚሆነው ሁለት ሐሳብ ስላለውና በመንገዱም ስለሚያወላውል ነው።


እናንተ ከዳተኞች! ዓለምን የሚወድ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑን አታውቁምን? እንግዲህ ዓለምን የሚወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑ ነው።


ዓለምን ወይም የዓለምን ነገር ሁሉ አትውደዱ። ዓለምን የሚወድ እግዚአብሔር አብን አይወድም።


በተከታዩም ቀን ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ የምስሉ ሐውልት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እንደገና ወድቆ አዩት፤ በዚህ ጊዜ ራሱና ሁለት እጆቹ ተሰባብረው በመግቢያው መድረክ ላይ ወድቀው ሌላው አካሉ ብቻ ቀርቶ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos