Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 11:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ክፉ ሰው የሐሰት ደመወዝ ያገኛል፥ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋ አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ክፉ ሰው የሚያገኘው ትርፍ መቅኖ የለውም፤ ጽድቅን የሚዘራ ግን አስተማማኝ ዋጋ ያገኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ክፉ ሰዎች የሚያገኙት ጥቅም አይኖርም፤ ትክክል የሆነውን ነገር ብታደርግ፥ የመልካም ሥራህን ዋጋ ታገኛለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ክፉ ሰው የበደልን ሥራ ይሠራል፤ ለጻድቃን ዘር ግን የታመነ ዋጋ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 11:18
15 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም ለአዋላጆቹ መልካም ነገርን አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዛ፥ እጅግም ብርቱ ሆነ።


እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ፥ በነፍሳቸውም ላይ ይሸምቃሉ።


የጻድቅ ደመወዝ ለሕይወት ነው፥ የክፉ ገቢው ግን ለኃጢአት ነው።


ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የቁጣውም በትር ይጠፋል።


ክፉ በክፋቱ ይጠመዳል፥ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ቅጥርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች።


ልባቸው ሐሰተኛ ነው፤ በደላቸውን አሁን ይሸከማሉ፤ ጌታ መሠዊያዎቻቸውን ይሰባብራል፥ ሐውልቶቻቸውን ያጠፋል።


የሚያጭድ ደመወዝን ይቀበላል፤ የሚዘራና የሚያጭድም አብረው ደስ እንዲላቸው ለዘለዓለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል።


ስለ ቀድሞ አኗኗሯችሁም፥ በሚያታልል ምኞቱ የጎደፈውንና የተበላሸውን፥ አሮጌ ሰው አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤


የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos