ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
ዘፍጥረት 12:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፤ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ። |
ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠራና እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ላይ፥ ከእንጨቱ በላይ አጋደመው።
ከአባቴ ቤት ከተወለድሁባት ምድርም ያወጣኝ፦ ‘ይህችንም ምድር ለዘርህ እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፥ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።
በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም፥ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።
እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ፦ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፥
ስደተኛ ሆነህ የተቀመጥህባትን እግዚአብሔርም ለአብርሃምን የሰጣትን ምድር ትወርስ ዘንድ የአብርሃም በረከት ለአንተ ይስጥህ፥ ለዘርህም እንዲሁ።”
በዚያም መሠዊያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም “ኤልቤቴል” ብሎ ጠራው፥ እርሱ ከወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።
ዮሴፍም ወንድሞቹን፦ “እኔ እሞታለሁ፥ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፥ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል” አላቸው።
ኖኅም ለጌታ መሠውያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዓይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው።
በዚያም ዳዊት ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት አቀረበ። ከዚያም ጌታ ለምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም መቅሰፍት ቆመ።
አምላካችን ሆይ! በዚህ ምድር የነበሩትን አሕዛብ ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት ያሳደድህ፥ ለወዳጅህም ለአብርሃም ዘር ለዘለዓለም የሰጠሃት አንተ አይደለህምን?
የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ ተነሣ፥ ወንድሞቹ ካህናትና፥ የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤልና ወንድሞቹም በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሊያቀርቡበት የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።
‘ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም ምድር ሁሉ እንደተናገርሁት ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘለዓለምም ይወርሱአታል’ ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባርያዎችህን አብርሃምን፥ ይስሐቅንና እስራኤልን አስብ።”
ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ሂድ፥ አንተ ከግብጽ ምድር ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’ ብዬ ወደ ማልሁባት ምድር ውጣ፤
ደግሞም የከነዓንን ምድር፥ በእንግድነት ተቀምጠውበት የነበረውን የእንግድነታቸው ምድር እሰጣቸው ዘንድ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳኔን መሰረትኩ።
በዚያም ዘመን የይሁዳ ቤት ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳሉ፤ በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
‘ከግብጽ የወጡት ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ ያሉት ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ለመስጠት የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤
በዚችም የእግር ጫማ ስንኳ የሚያህል ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን ልጅ ሳይኖረው ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ ሰጠው።
የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር። ለብዙዎች እንደሆነ “ለዘሮችህ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ እንደሆነ “ለዘርህም” ይላል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።
እነሆ፥ ምድሪቱን በፊታችሁ አኖራለሁ፥ ግቡ፥ ጌታ ለእነርሱ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውንም ምድር ውረሱ።’
ጌታ አምላክህን ውደደው፤ ለቃሉም ታዘዝ፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቅ። ጌታ ለአባቶችህም ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር የዕድሜህም ዘመን ሕይወትም ማለት ነው።”
ጌታም፦ “ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት፥ በዓይንህ እንድታያት አደረግሁህ፥ ነገር ግን ወደዚያች አትሻገርም” አለው።
“ጌታ አምላክህ ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ፥ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባስገባህ ጊዜ፥ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥
ምድራቸውን እንድትወርስ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፥ ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ ሕዝቦች ኃጢአት ምክንያትና፥ ለአባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብ፥ ጌታ የማለላቸውን ቃል እንዲፈጸም ነው።
እነዚህ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ሳያገኙ እምነታቸውን እንደ ጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከርቀት አይተውት ሰላምታ አቀረቡለት፤ በዚህ ምድር ሲኖሩም እንግዶችና መጻተኞች ለመሆንም ታመኑ።
በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዮርዳኖስ አጠገብ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ።
ጌዴዎንም በዚያ ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “ጌታ ሰላም ነው” ብሎ ጠራው፤ ይህ መሠዊያ የአቢዔዝራውያን ይዞታ በሆነው በዖፍራ ዛሬም ቆሞ ይታያል።