Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 24:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሙሴም የጌታን ቃሎች ሁሉ ጻፈ፤ በማለዳ ተነሥቶ ከተራራው በታች መሠዊያንና ዐሥራ ሁለት ሐውልቶች ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ሙሴ እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ ጻፈ። በማግስቱም ማልዶ ተነሥቶ፣ በተራራው ግርጌ መሠዊያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤልን ነገዶች የሚወክሉ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሙሴም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጻፈ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ በተራራው ሥር መሠዊያ ሠራ፤ ለእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንድ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሙሴም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለ​ዳም ተነሣ፤ ከተ​ራ​ራ​ውም በታች መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ድን​ጋ​ዮ​ችን ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ አቆመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ ማለዳም ተነሣ፥ ከተራራውም በታች መሠዊያን፥ አሥራ ሁለትም ሐውልቶች ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 24:4
27 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።


ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ፥ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት።


ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፥ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከዐሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።”


ያዕቆብም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አቆመ።


አኪያም የለበሰውን አዲስ መጐናጸፊያ አውልቆ ከዐሥራ ሁለት ቆራረጠው።


ጌታ ከዚያ በፊት “እስራኤል” ብሎ ከሰየመው ከያዕቆብ በተወለዱት በዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ወሰደ።


ለዚህ የእግዚአብሔር ቤት ምረቃ አንድ መቶ ወይፈኖች፥ ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶ የበግ ጠቦቶችን፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት እንደ እስራኤል ነገዶች ቍጥር ለእስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ።


በዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፤ መሪዎቻችን፥ ሌዋውያኖቻችንና ካህናቶቻችን ያትሙበታል።


ጌታም ሙሴን፦ “ይህንን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ አኑረው፥ የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና” አለው።


ሙሴም መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም “ጌታ ሰንደቅ ዓላማዬ ነው” ብሎ ጠራው፤


“በፊታቸው የምታኖረው ሥርዓት ይህ ነው።


የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ በሕዝቡ ጆሮ ላይ አወጀ፤ እነርሱም፦ “ጌታ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም” አሉ።


የዕንቁ ድንጋዮች እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች ዐሥራ ሁለት ይሆናሉ፤ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ማኅተም እንደሚቀረጽ በየስማቸው ይቀረጹ።


ጌታም ሙሴን፦ “በእነዚህ ቃሎች መጠን ከአንተና ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን አድርጌአለሁና እነዚህን ቃሎች ጻፍ” አለው።


በዚያ ቀን በግብጽ ምድር መካከል ለጌታ መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ለጌታ ዓምድ ይቆማል።


“መልካሙንም ዱቄት ውሰድ፤ በእርሱም ዐሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር፤ በአንድ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ይደረግበት።


“ለእስራኤል ልጆች ተናገር፥ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸው ሁሉ ከየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፥ ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ።


በመንግሥቴም ከእኔ ማዕድ ትበላላአችሁ፥ እንዲሁም ትጠጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይም ለመፍረድ በዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ።


የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ ምሰሶዎች መስለው የሚታዩ ያዕቆብ፥ ኬፋና ዮሐንስ፥ እነርሱ ወደ ተገረዙት እኛ ወደ አሕዛብ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ የኅብረት ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤


ሙሴም ይህን ሕግ ጽፎ፥ የጌታን የኪዳን ታቦት ለሚሸከሙ ለሌዊ ልጆች፥ ለካህናቱና ለእስራኤል አለቆች ሁሉ ሰጠ።


ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን እነዚያን ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አኖራቸው።


ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በጌታ ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል እለፉ፤ ከእናንተም ሰው ሁሉ በእስራኤል ልጆች ነገድ ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም።


ለከተማይቱም ቅጥር ዐሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፤ በእነርሱም ውስጥ የዐሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos