ከእርሷ በበላችሁ ቀን ዐይኖቻችሁ እንደሚከፈቱ፥ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።”
ሕዝቅኤል 28:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለጢሮስ ገዥ እንዲህ በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ልብህ በትዕቢት ተወጥሮ፣ “እኔ አምላክ ነኝ፤ በአምላክ ዙፋን ላይ፣ በባሕሮችም ልብ ተቀምጫለሁ” አልህ። ምንም እንኳ እንደ አምላክ ጠቢብ ነኝ ብለህ ብታስብም፣ አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ልብህ ስለ ታበየ እኔ አምላክ ነኝ በባሕሩ መካከል በአማልክት ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ ብለሃል። ምንም እንኳ አንተ በሐሳብህ አምላክ ነኝ ብትል ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስን አለቃ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርትዋል፥ አንተ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እግዚአብሔርም በባሕር መካከል እንዲቀመጥ እኔም ተቀምጫለሁ ብለሃልና፤ አንተ ሰው ስትሆን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ እግዚአብሔር አይደለህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር መካከል ተቀምጫለሁ ብለሃል፥ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም። |
ከእርሷ በበላችሁ ቀን ዐይኖቻችሁ እንደሚከፈቱ፥ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።”
ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ ጌታ እጁን በሚዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፥ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
አሁንም አንቺ ተድላን የምትወጅ፥ በምቾትም የምትቀመጪ፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፥ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ ይህን ስሚ፤
እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነበር፤ በእርሷና በሴቶች ልጆቿ ትዕቢት፥ የምግብ ጥጋብ፥ የበለጸገ ምቾት ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።
በአንቺ ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፥ እንዲህም ይሉሻል፦ ከባሕር የተቀመጥሽ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ ዝነኛ ከተማ ሆይ፥ እንዴት ጠፋሽ!
እንዲህም ብለህ ተናገር፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “‘ወንዙ የእኔ ነው እኔ ራሴ ሠርቼዋለሁ’ የምትል፥ በወንዞች መካከል የምትተኛ፥ አንተ ታላቅ ድራጎን የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።
ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።
እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።
በመንፈስም ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶችም ባሉት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
ራስዋን በአከበረችበትና በተቀማጠለችበት ልክ ሥቃይንና ኀዘንን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ መበለትም አልሆንም፤ ኀዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥