ሕዝቅኤል 28:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በውበትህ ምክንያት፣ ልብህ ታበየ፤ ከክብርህ ታላቅነት የተነሣም፣ ጥበብህን አረከስህ። ስለዚህ ወደ ምድር ወረወርሁህ፤ ለነገሥታት ትዕይንት አደረግሁህ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 መልከ ቀና በመሆንህ እጅግ ታብየህ ነበር፤ ክብር በመፈለግህም ጥበብን አቃለልክ፤ ከዚህም የተነሣ አምዘግዝጌ ወደ መሬት ጣልኩህ፤ ለሌሎች ነገሥታትም የመቀጣጫ ምልክት አደረግሁህ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ፤ ያዩህም፥ ይዘብቱብህም ዘንድ በነገሥታት ፊት አሳልፌ ሰጠሁህ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፥ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፥ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ። Ver Capítulo |