ኢሳይያስ 47:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 አሁንም አንቺ ተድላን የምትወጅ፥ በምቾትም የምትቀመጪ፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፥ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ ይህን ስሚ፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 “አሁንም አንቺ ቅምጥል ፍጡር፣ በራስሽ ተማምነሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም፤ ከእንግዲህ መበለት አልሆንም፤ የወላድ መካንም አልሆንም’ የምትይ ስሚ! Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 “አንቺ በልብሽ ‘እንደ እኔ ያለ ማንም የለም፤ ባልዋ እንደ ሞተባት ሴት ሆኜ አልኖርም፤ ወይም የልጅ ሞት አይደርስብኝም’ ብለሽ በመዝናናት የተቀመጥሽው ቅምጥሊቱ ሆይ! ይህን ስሚ፦ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፥ በልብሽም፥ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፤ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ፥ ይህን ስሚ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፥ በልብሽም፦ እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፥ መበለትም ሆኜ አልኖርም የወላድ መካንነትንም አላውቅም የምትዪ ይህን ስሚ፥ Ver Capítulo |