Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 31:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በቁመት ረዝመሃል፥ ጫፉን በቅርንጫፎች መካከል አድርጎአልና፥ ልቡም በቁመቱ ኰርቶአልና፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጥቅጥቅ ባለው ቅጠል ላይ ጫፉን ከፍ በማድረግ ራሱን በማንጠራራቱ፣ በርዝማኔውም በመኵራራቱ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “እንግዲህ አድጎ እስከ ደመናት በደረሰ መጠን፥ ትዕቢት በሚሰማው በዚያ ዛፍ ላይ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የማደርገው ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ቁመ​ትህ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ ራስ​ህም በደ​መ​ናት መካ​ከል ደር​ሶ​አ​ልና፤ ትዕ​ቢ​ቱ​ንም አየሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቁመትህ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ ራሱንም በደመናዎች መካከል አድርጎአልና፥

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 31:10
16 Referencias Cruzadas  

አንተም፦ ‘እነሆ፥ ኤዶምያስን መትቻለሁ’ ብለህ ኰርተሃል፤ በቤትህ ተቀመጥ፤ አንተ ከይሁዳ ጋር አብረህ ለመውደቅ ለምን መከራ ትሻላህ?”


ሕዝቅያስ ግን እንደ ተቀበለው ቸርነት መጠን አላደረገም፥ ልቡም ኰራ፤ ስለዚህም በእርሱና በይሁዳ በኢየሩሳሌምም ላይ ቁጣ ሆነ።


ትዕቢት ጥፋትን፥ ኩሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።


ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።


ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤


በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።


ወደ ጉድጓድ በሚወርዱ በሰው ልጆች መካከል ሁላቸው ለታችኛው ምድር ለሞት አልፈው ተሰጥተዋልና በውኃ አጠገብ ያሉ ዛፎች ሁሉ በቁመታቸው እንዳይረዝሙ፥ ራሳቸውንም በደመናዎች መካከል እንዳያደርጉ፥ ውኃንም የሚጠጡ ኃያላኖቻቸው ሁሉ በቁመታቸው እንዳይቆሙ።


እነሆ አሦር ቅርጫፉ የተዋበ፥ ጥላ የሚሰጥ ጫካ፥ ቁመቱ የረዘመ፥ ጫፉም በቅርንጫፎች መካከል የነበረ የሊባኖስ ዝግባ ነበረ።


በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ራሱንም ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ከፍ ይላል።


ስለዚህ፥ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” እንደሚል፥ የሚሰጠው ጸጋ ግን ከሁሉም ይበልጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos